ኢኢግልድ ስትራቴጂክ ዕቅዱና ሌሎችም የአሰራር ስርዓቶቹን ገመገመ

10/05/2024

ኢኢግልድ በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ላይ ተሳተፈ

09/05/2024

ኢኢግልድ 10ኛው አገር ዓቀፍ የሕብረት ሥራ ማሕበራት ኤግዚቢሽንና ባዛር ተሳተፈ

15/02/2024

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በኢኢግልድ ጉብኝት አካሄዱ

29/01/2024

የአመራሮችና የባለሙያዎች ቅንጅትና የስራ ትጋት ለድርጅቱን አፈጻጸም ውጤታማነት ሚና እንደሚኖረው ተገለጸ

17/01/2024

ማስታወቂያ

27/11/2023

የምግብ ዘይት በቫይታሚን ለማበልጸግ የሚያስፈልገውን የፕሪሚክስ አቅርቦትን አስመልክቶ የወጣ ማስታወቂያ

06/11/2023

ኢኢግልድ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ገመገመ

06/11/2023

ማስታወቂያ

25/10/2023

ኢኢግልድ የ4.2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አበረከተ

17/10/2023

ኢኢግልድ የ16.5 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት በተመጣጣኝ ዋጋ አቀረበ

14/09/2023

ኢኢግልድ የዲስትሪክቶችን የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የቀጣይ ዓመት ዕቅድ ግምገማ አካሄደ

23/08/2023

የኢኢግልድ ሥራ አመራር ቦርድ አባላት በግንባታ ላይ የሚገኙና ግንባታቸው የተጠናቀቁ ፕሮክቶችን ጎበኙ

31/07/2023

ኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኞች የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አካሄዱ

27/07/2023

የኢኢግልድ ሴት ሠራተኞች ፎረም ተመሰረተ

20/07/2023

ኢኢግልድ የ2015 በጀት ዓመት የስምንት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ

11/04/2023

ኢኢግልድ ለ33 የድርጅቱ ባለሙያዎች የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ልማትና ትግበራ ስልጠና ሠጠ

23/03/2023

ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ ፕሮጀክቶች ግንባታ ገብኝት ተካሄደ

18/01/2023

አርአያነት ያለው ተግባር

14/09/2022

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የፍጆታ ምርቶች መሸጫ ዋጋ

09/09/2022

— 20 Items per Page
Showing 1 - 20 of 37 results.

የአመራሮችና የባለሙያዎች ቅንጅትና የስራ ትጋት ለድርጅቱን አፈጻጸም ውጤታማነት ሚና እንደሚኖረው ተገለጸ

አመራሮችና ባለሙያዎች ድርጅቱ ያቀዳቸውን ግቦች ውጤታማ ለማድረግ በቅንጅትና በትጋት ሊሰሩ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ ክብርት ወ/ሮ የሺመቤት ነጋሽ ከጥር 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት በቢሾፍቱ ከተማ የድርጅቱ የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ማጠናቀቂያ ላይ አስታወቁ፡፡

አያይዘውም ድርጅቱ በንግዱ ዘርፍ ያለውን የረጅም ዓመት ተሳትፎ የካበተ የአመራሮችና የባለሙያዎች ልምድና አቅም እንዲሁም በመላ አገሪቱ የሚገኙ ከ80 በላይ የሽያጭ ቅርንጫፎቻችንን ተደራሽነት በማቀናጀት አጥጋቢ ውጤት ማምጣት እንደሚቻልም አሳስበዋል፡፡

በተለይም ድርጅቱ የተሰማራበትን አምራች ኢንዱስትሪዎችን በግብዓት አቅርቦት የመደገፍና በሸቀጦች አቅርቦት ገበያውን ለማረጋጋት እየሰራ ካለው ተግባራት አንጻር መንግስት ለድርጅቱ እየሰጠ ያለውን የሥራ ማስፈጻሚያ ካፒታል ድጋፍ እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም የድርጅቱ አመራሮችና ባለሙያዎች ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ በግምገማው ማጠናቀቂያ ላይ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ባመላከቱበት ወቅት ተገልጿል፡፡

የድርጅቱ የበላይና መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም የቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ለሶስት ቀናት የውይይትና የግምገማ መድረክ በኢንዱስትሪ ግብዓቶችና ውጤቶች ግዢ፣ ሽያጭ፣አቅርቦትና ስርጭት አፈጻጸም፣ የድርጅቱን አሠራር ለማዘመን እየተተገበሩ የሚገኙ ቴክኖሎጂዎች ትግበራና ተግዳሮቶች፣ የገበያ ጥናትና የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ፣ የድርጅቱ ሀብትና ንብረት አስተዳደር ፣ እንዲሁም ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገባ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተደርጎ ውይይት ግምገማ ተካሂዶ የጋራ መግብብት ላይ ተደርሷል፡፡