ኢኢግልድ በስትራቴጂክ ዕቅዱና በአሰራር መመሪያዎች ረቂቅ ላይ ሲያካሂድ የነበረውን ግምገማ አጠናቀቀ

13/05/2024

ኢኢግልድ ስትራቴጂክ ዕቅዱና ሌሎችም የአሰራር ስርዓቶቹን እየገመገመ ይገኛል

10/05/2024

ኢኢግልድ በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ላይ ተሳተፈ

09/05/2024

ኢኢግልድ 10ኛው አገር ዓቀፍ የሕብረት ሥራ ማሕበራት ኤግዚቢሽንና ባዛር ተሳተፈ

15/02/2024

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በኢኢግልድ ጉብኝት አካሄዱ

29/01/2024

የአመራሮችና የባለሙያዎች ቅንጅትና የስራ ትጋት ለድርጅቱን አፈጻጸም ውጤታማነት ሚና እንደሚኖረው ተገለጸ

17/01/2024

ማስታወቂያ

27/11/2023

የምግብ ዘይት በቫይታሚን ለማበልጸግ የሚያስፈልገውን የፕሪሚክስ አቅርቦትን አስመልክቶ የወጣ ማስታወቂያ

06/11/2023

ኢኢግልድ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ገመገመ

06/11/2023

ማስታወቂያ

25/10/2023

ኢኢግልድ የ4.2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አበረከተ

17/10/2023

ኢኢግልድ የ16.5 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት በተመጣጣኝ ዋጋ አቀረበ

14/09/2023

ኢኢግልድ የዲስትሪክቶችን የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የቀጣይ ዓመት ዕቅድ ግምገማ አካሄደ

23/08/2023

የኢኢግልድ ሥራ አመራር ቦርድ አባላት በግንባታ ላይ የሚገኙና ግንባታቸው የተጠናቀቁ ፕሮክቶችን ጎበኙ

31/07/2023

ኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኞች የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አካሄዱ

27/07/2023

የኢኢግልድ ሴት ሠራተኞች ፎረም ተመሰረተ

20/07/2023

ኢኢግልድ የ2015 በጀት ዓመት የስምንት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ

11/04/2023

ኢኢግልድ ለ33 የድርጅቱ ባለሙያዎች የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ልማትና ትግበራ ስልጠና ሠጠ

23/03/2023

ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ ፕሮጀክቶች ግንባታ ገብኝት ተካሄደ

18/01/2023

አርአያነት ያለው ተግባር

14/09/2022

— 20 Items per Page
Showing 1 - 20 of 38 results.

ኢኢግልድ የዲስትሪክቶችን የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የቀጣይ ዓመት ዕቅድ ግምገማ አካሄደ

 

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት(ኢግልድ) የዲስትሪክቶች የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም የተለያዩ ውስጣዊና ውጪያዊ ተግዳሮቶች ቢያጋጥሙትም ጥሩ ውጤትና የሚያበረታታ አፈጻጸም የተመዘገበበት መሆኑን የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ የሺመቤት ነጋሽ ገለጹ፡፡

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ይህንን የገለጹት የድርጅቱ የበጀት ዓመት አፈጻጸምና ዕቅድ እንዲሁም የዲስትሪክቶች የበጀት ዓመቱ አፈጻጸምና ዕቅድ ግምገማና ውይይት ከነሐሴ 13-14/2015 ዓ.ም በግዮን ሆቴል የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡

አያይዘውም የድርጅቱ አፈጻጸም አበረታች ቢሆንም በአፈጻጸም ወቅት የታዩ ክፍተቶች ተለይተው በቀጣይ በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ የሚታረሙበት የአሰራር ሥርዓት ተዘርግተውላቸው አጥጋቢ ውጤት ለማስመዝገብ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡

በዚሁ መድረክ የማዕከላዊ፣ የምስራቅ፣ የምዕራብና የደቡብ ዲስትሪክቶች ሥር የሚገኙ የሽያጭ ቅርንጫፎች ዕቅድ አፈጻጸምና የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ በዲስትሪክቶቹ ሃላፊዎች እንዲሁም የድርጅቱ የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የ2016 ዕቅድ በስትራቴጂክ ሥራ አመራር ዳይሬክተር ቀርቦ ግምገማና ውይይት ተካሂዶ የጋራ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ ተሰርቷል፡፡

በሁለቱ ቀናት  ውይይት ዲስትሪክቶች ከዕቅድ እስከ አፈጻጸም ተናበው ለመስራት ያደረጓቸው ጥረቶችና የተገኙ ውጤቶች(የታዩ ክፍተቶች እንዳሉ ሆነው)አበረታች መሆናቸው፣ ሁሉም ዲስትሪክቶች ዕቅዶቻቸውን ከኮርፖሬት ዕቅዱ ጋር በመናበብ ለመፈጸም ያደረጉት ጥረት ሊበረታታ የሚገባው እንደሆነ፣ በሽያጭ ቅርንጫፎቻችን የሚገኙ የሸቀጦች ክምችት ጋር በተያያዘ ነባሩ አሠራር ትኩረት ሊሰጠውና ሊሻሻል እንደሚገባ፣ ለደንበኞች የተሠጠው ትኩረት ካለፉት ዓመታት የተሻለ ቢሆንም አሁንም ትኩረት ተሰጥቶት መሰራት እንዳለበትና ሌሎችም ዓበይት ጉዳዮች ተነስተው የጋራ ግንዛቤ የተጨበጠባቸው ሲሆን ለግብዓት ግዢ የተገኘውን ብድር በጥቅም ላይ ማዋል፣ የድርጅቱ የሒሳብ ምርመራ፣ እየተገበሩ የሚገኙ ፕሮጀክቶች እና የሪፎርም ሥራዎች ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች እንደሆኑ ተብራርቷል፡፡

በሁለቱ ቀናት በአዳራሽ ከተካሄደው የውይይት በተጨማሪ የበላይ አመራሮች፣ የዲስትሪክት ሃላፊዎችና ባለሙያዎች በግንባታ ላይ የሚገኘውን ባለ 18 ወለል የዋና መ/ቤት ሕንፃ ፕሮጀክት እንዲጎበኙና በፕሮጀክቱ የሚገኝበትን ደረጃ እንዲረዱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ማብራሪያ  በፕሮጀከቱ ሃላፊ  ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል፡