ስለ ኢግልድ
ተልዕኮ
- በብቁ የሰው ሀይልና ቴክኖሎጂ በተደገፈ የአሰራር ስርዓት በመታገዝ እና ጠንካራ የአቅርቦትና ግብይት ሰንሰለት በመፍጠር ጥራታቸውን የጠበቁ የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን በማልማት በማቅረብ እና የተመረጡ የኢንዱስትሪ ውጤቶችን ለተጠቃሚዎች ተደራሽ በማድረግ የሀገሪቱ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ውጤታማ እንዲሆኑ አስተዋጽኦ ማድረግና ገበያ ማረጋጋት ነው፡፡
ራዕይ
- በ2022 በአፍሪካ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ግብዓትና ውጤት ግብይት ተመራጭ የቢዝነስ አጋር ሆኖ መገኘት
እሴቶች
- ደንበኛ ተኮር
- ቅደሚያ ለጥራት
- ተጠያቂነት
- ታማኝነት
- የቡድን ስራ
- ምርታማነት
ተግባርና ኃላፊነቶች
- የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን አቅርቦት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ድርጅቶችን መገንባት፤ ማስተዳደር እንዲሁም አስፈላጊ ሲሆን ማስተላለፍ፤
- በአገር ውስጥና በውጭ አገር የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን በማምረት ማቅረብ፤
- የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን ከአገር ውስጥና ከውጭ አገር በመግዛት ማቅረብ፤
- ከአገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች ፍጆታ በላይ የሆኑትን የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ወደ ውጭ አገር መላክ፤
- የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት እና ጥሬ ዕቃ በማቅረብ በሥራ ላይ ከተሰማሩ ድርጅቶች ጋር በጋራ መስራት፤
- ቀልጣፋና ውጤታማ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ለማረጋገጥ የሚያስችል ጠንካራ የአቅርቦት ሰንሰለት ማኔጅመንት መተግበር፤
- ተመሳሳይ ዓላማ ካላቸው በአገር ውስጥና በውጭ አገር ከሚገኙ የግልና የመንግስት ተቋማት ጋር ትብብር ማድረግ፤
- በዋስትና የማስያዝና ከአገር ውስጥና ከውጭ የገንዘብ ምንጮች ጋር የብድር ውል የመደራደርና የመፈራረም፤
- ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ የሆኑ ሥራዎችን ማከናወን፣ እና በተጨማሪ በደንቡ በአንቀፅ 11 በተሰጠው የአቅርቦት ክፍተቶችን ለሟሟላት፣ የድርጅቱን የገቢ ምንጭ ለማስፋትና ገበያን ለማረጋገት የኢንዱስትሪ ውጤቶችን ለሽያጭ የማቅረብ ተግባራት ማከናወን ይሆናል፡፡
13181 Views
1 የሸቀጦች ጅምላ ንግድ አስመጪ ድርጅት(ከ1928-2007)
ከተመሰረተ ከሰባት አስርት ዓመታት በላይ የስቆጠረው የሸቀጦች ጅምላ ንግድ አስመጪ ድርጅት (ጅንአድ) ቀደም ባሉት ዓመታት የተለያዩ ስያሜዎችን በመያዝ በተለያዩ የመንግስት ስርዐቶች ውስጥ የዘለቀና በተለያዩ የፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ስርዓቶች ሲከተሉ በነበሩ የመንግስት መዋቅር ውስጥ ተፈትኖ ያለፈና አሁን የሚገኝበት ደረጃ ላይ የሚገኝ ድርጅት ነው፡፡
ጅንአድ በ1928 ዓ.ም የ ውጭ...