ኢኢግልድ ስትራቴጂክ ዕቅዱና ሌሎችም የአሰራር ስርዓቶቹን እየገመገመ ይገኛል

10/05/2024

ኢኢግልድ ስትራቴጂክ ዕቅዱና ሌሎችም የአሰራር ስርዓቶቹን እየገመገመ ይገኛል

10/05/2024

ኢኢግልድ በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ላይ ተሳተፈ

09/05/2024

ኢኢግልድ 10ኛው አገር ዓቀፍ የሕብረት ሥራ ማሕበራት ኤግዚቢሽንና ባዛር ተሳተፈ

15/02/2024

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በኢኢግልድ ጉብኝት አካሄዱ

29/01/2024

የአመራሮችና የባለሙያዎች ቅንጅትና የስራ ትጋት ለድርጅቱን አፈጻጸም ውጤታማነት ሚና እንደሚኖረው ተገለጸ

17/01/2024

ማስታወቂያ

27/11/2023

የምግብ ዘይት በቫይታሚን ለማበልጸግ የሚያስፈልገውን የፕሪሚክስ አቅርቦትን አስመልክቶ የወጣ ማስታወቂያ

06/11/2023

ኢኢግልድ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ገመገመ

06/11/2023

ማስታወቂያ

25/10/2023

ኢኢግልድ የ4.2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አበረከተ

17/10/2023

ኢኢግልድ የ16.5 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት በተመጣጣኝ ዋጋ አቀረበ

14/09/2023

ኢኢግልድ የዲስትሪክቶችን የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የቀጣይ ዓመት ዕቅድ ግምገማ አካሄደ

23/08/2023

የኢኢግልድ ሥራ አመራር ቦርድ አባላት በግንባታ ላይ የሚገኙና ግንባታቸው የተጠናቀቁ ፕሮክቶችን ጎበኙ

31/07/2023

ኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኞች የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አካሄዱ

27/07/2023

የኢኢግልድ ሴት ሠራተኞች ፎረም ተመሰረተ

20/07/2023

ኢኢግልድ የ2015 በጀት ዓመት የስምንት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ

11/04/2023

ኢኢግልድ ለ33 የድርጅቱ ባለሙያዎች የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ልማትና ትግበራ ስልጠና ሠጠ

23/03/2023

ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ ፕሮጀክቶች ግንባታ ገብኝት ተካሄደ

18/01/2023

አርአያነት ያለው ተግባር

14/09/2022

— 20 Items per Page
Showing 1 - 20 of 38 results.

ኢኢግልድ ለ33 የድርጅቱ ባለሙያዎች የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ልማትና ትግበራ ስልጠና ሠጠ

ኢኢግልድ ለ33 የድርጅቱ ባለሙያዎች የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ልማትና ትግበራ ስልጠና ሠጠ

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ልማትና ትግበራ ጋር በተያያዘ ከተለያዩ የሥራ ክፍሎች ለተውጣጡ 33 የድርጅቱ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች በቢሻፍቱ ከተማ ከመጋቢት 4-8 2015 ዓ.ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡

ለአምስት ቀናት የተሰጠው ስልጠና የድርጅቱን የአሰራር ሥርዓት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመጣጣኝና ዘመናዊ በማድረግ ኢኢግልድን ተወዳዳሪና ውጤታማ ለማድረግ የታቀደ ሲሆን በኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት አማካሪነት የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ልማትና ትግበራው ክትትል እንደሚከሄድም ታውቋል፡፡

ከዚህ ሥልጠና ቀደም ባሉት ጊዜያት ከጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት አንጻር በድርጅታችን ዋናው መስሪያ ቤት እና በዲስትሪክቶች በመገኘት መረጃዎችን በማሰባሰብ፣ ትንተና በማካሄድ የአሰራር ሥርዓት ክፍተት (Gap assessment) ተለይቶ የጥናት ሪፖርቱ ለማኔጅመንት የቀረበ ሲሆን ስለ ጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ገለጻ ተደርጎ በድርጅታችን ማኔጅመንቱ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በመሆኑም ለጥራት ስራ አመራር ስርዓቱ ልማትና ትግበራ የጥራት አስተባባሪ የተመደበ ሲሆን የአሰራር ስርዓቱን ለመተግበር እንዲቻል ከሁሉም የሥራ ክፍሎች የተውጣጡ 33 አባላትን ያካተተ ግብረ-ኃይል ተመርጦ ወደ ስልጠናው ተገብቷል፡፡

በቀጣይም በተመሳሳይ ዘርፍ የተሰማሩ ሆነው የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓትን ተግባራዊ ካደረጉ ድርጅቶች የልምድ ልውውጥ ማድረግ፣ እንዲሁም የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓትን ትግበራ ዕውን ለማድረግ የሚያስፈልጉ መመሪያዎችን፣ ፕሮሲጀር ማንዋሎችን፣ የሥራ መመሪያዎች፣ ቅጾችን እና ሌሎች ዶክመንቶችን በመለየት የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓትን ለመተግበር የሚያስፈልጉ ዶክመንቶች እንዲዘጋጁ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

ከዚህ አንጻር በየሥራ ክፍሎች መመሪያዎች፣ ፕሮሲጀር ማንዋሎችን፣ የሥራ መመሪያዎች፣ ቅጾችን እና ሌሎች ዶክመንቶችን በመለየት በጥራት ሥራ አመራር አሠራር ሥርዓት መርህ መሠረት ተግባራዊ በማድረግ ድርጅታችን ተወዳዳሪና ውጤታማ በማድረግ፤ የአምራች ኢንዱስትሪዎችን እንዲሁም የገበያ ማረጋጋት ሥራን ውጤታማ በሆነ አሰራር በመምራት ድርጅቱን ተወዳዳሪ፣ ውጤታማ እና ትርፋማ በማድረግ ለአገራችን ኢኮኖሚ ዕድገት የበኩሉን ሚና የሚወጣ ተቋም ለማድረግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡