የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በኢኢግልድ ጉብኝት አካሄዱ

29/01/2024

የአመራሮችና የባለሙያዎች ቅንጅትና የስራ ትጋት ለድርጅቱን አፈጻጸም ውጤታማነት ሚና እንደሚኖረው ተገለጸ

17/01/2024

ማስታወቂያ

27/11/2023

የምግብ ዘይት በቫይታሚን ለማበልጸግ የሚያስፈልገውን የፕሪሚክስ አቅርቦትን አስመልክቶ የወጣ ማስታወቂያ

06/11/2023

ኢኢግልድ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ገመገመ

06/11/2023

ማስታወቂያ

25/10/2023

ኢኢግልድ የ4.2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አበረከተ

17/10/2023

ኢኢግልድ የ16.5 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት በተመጣጣኝ ዋጋ አቀረበ

14/09/2023

ኢኢግልድ የዲስትሪክቶችን የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የቀጣይ ዓመት ዕቅድ ግምገማ አካሄደ

23/08/2023

የኢኢግልድ ሥራ አመራር ቦርድ አባላት በግንባታ ላይ የሚገኙና ግንባታቸው የተጠናቀቁ ፕሮክቶችን ጎበኙ

31/07/2023

ኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኞች የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አካሄዱ

27/07/2023

የኢኢግልድ ሴት ሠራተኞች ፎረም ተመሰረተ

20/07/2023

ኢኢግልድ የ2015 በጀት ዓመት የስምንት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ

11/04/2023

ኢኢግልድ ለ33 የድርጅቱ ባለሙያዎች የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ልማትና ትግበራ ስልጠና ሠጠ

23/03/2023

ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ ፕሮጀክቶች ግንባታ ገብኝት ተካሄደ

18/01/2023

አርአያነት ያለው ተግባር

14/09/2022

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የፍጆታ ምርቶች መሸጫ ዋጋ

09/09/2022

የኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኞች የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ በላቀ ሁኔታ ለመፈጸም ዝግጁ መሆናቸውን አስታወቁ

29/08/2022

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት አመራሮችና ሠራተኞች ለአቅመ ደካሞች የቤት ዕድሳት የማስጀመር እና የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ አከናወኑ

07/08/2022

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት በ9ኛው ሀገር አቀፍ የህብረት ስራ ኤግዚቢሽንና ባዛር ላይ በመሳተፍ ምርትና አገልግሎቱን አስተዋወቀ

09/02/2022

— 20 Items per Page
Showing 1 - 20 of 34 results.

ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ ፕሮጀክቶች ግንባታ ገብኝት ተካሄደ

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት(ኢኢግልድ) አመራሮችና ሠራተኞች ድርጅቱ በ2 ቢሊዮን ብር እያስገነባ ያለው የዋና መ/ቤት ህንጻና  ግንባታቸው የተጠናቀቁ 48 ለንግድ ሥራ የሚያገለግሉ ሱቆች ጉብኝት ጥር 9 ቀን 2015 ዓ.ም አካሄዱ፡፡
በአገራችን የተካሄደውን ለውጥ ተከትሎ ኢኢግልድ ውስጥ የሚታዩትን የአሰራርና አፈጻጸም እንዲሁም የመልካም አስተዳደርና የሙስና  ችግሮች ለመፍታት  በተወሰደው እርምጃ የአመራሮች ለውጥ በማካሄድና የተለያዩ የሪፎርም ሥራዎች በማከናወን ላይ የሚገኙ ሲሆን ከዚሁ ጋር በተያያዘ በተጨባጭ ውጤት የተገኘባቸው ሁለት ፕሮጀክቶች ተመርጠው በድርጅቱ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም ሠራተኞች እንዲጎበኙ ተደርገዋል፡፡
ድርጅቱ ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ መድቦ እያስገነባ የሚገኘው ባለ 18 ፎቅ የዋና መ/ቤት ህንጻ አንዱ ሲሆን ህንጻው ከዋና መ/ቤት ጽ/ቤት ባሻገር የተለያዩ አገልግሎት የሚሰጡ በተለይም ለባንክ፣  ሱፐር ከርኬት፣ ለጂምና ለተለያዩ አገልግሎቶች ሊውል ታቅዶ ግንባታው እተካሄደ እንደሆነ በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል፡፡
ከሜክሲኮ አደባባይ ዝቅ ብሎ አፍሪካ ፍብረት አካባቢ እየተገነባ የሚገኘው ይህ ህንጻ በሁለት ዓመታት ውስጥ የሚጠናቀቅ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የፕሮጀክቱ 46 በመቶ እንደተከናወነ እስከ 2015 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ የግንባታው 80 በመቶ እንደሚጠናቀቅ፤ ፕሮጀክቱ በዕቅዱ መሠረት እየተካሄደ እንደሚገኝ የፕሮጀክቱ አማካሪ ድርጅት አመልክቷል፡፡
በአመራሮችና ሠራተኞች ጉብኝት የተካሄደበት ሌላው ፕሮጀክት ግንባታቸው የተጠናቀቁና ለአገልግሎት ዝግጁ የተደረጉት በቃሊቲ ማዕከላዊ ዲስትሪክት የሚገኙት 48 ሱቆች ሲሆኑ ከዚህም በተጨማሪ ለቆዳ ውጤቶች ማምረቻ እንዲያገለግሉ የተገነቡትም ሼዶች  በዚሁ ወቅት ጉብኝት ተካተዋል፡፡
በቀጣይም ድርጅቱ በቆዳ ውጤቶች ላይ በማተኮር በቃሊቲ ማዕከላዊ ዲስትሪክት ባለ 4 ፎቅ ህንጻዎችን ለመገንባትና በቆዳ ውጤቶች ኤክስፖርት ንግድ ላይ ለመሰማራት እየሰራ እንደሚገኝም በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል፡፡
የኢኢግል ድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ የሺመቤት ነጋሽ በጉብኝቱ ማጠቃለያ ላይ እንደገለጹት ድርጅቱ የነበሩበትን የመልካም አስተዳደር ፣ የሙስና፣ ወቅቱን የዋጀ ዘመናዊ የአሰራርና የአፈጻጸም ችግሮች በመለየት የሪፎርም ስራዎች ተጠናክሮ እንዲሰራ በመደረጉ አሁን  ለተገኙት ውጤቶች አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን አመልክተዋል፡፡ 
በተካሄዱትም የሪፎርም ስራዎች  ድርጅቱን የሚመጥን መዋቅር በማስጠናት እንዲተገበር የተደረገ መሆኑን የገለጹት ወ/ሮ የሺመቤት  ቀድሞ የነበሩ መመሪያዎች  እንዲሻሻሉና 10 አዳዲስ መመሪያዎች ተዘጋጅተው   በድርጅቱ ስራ አመራር ቦርድ እንዲጸድቁ ተደርገው ወደስራ እንደተገባ፤ አሰራርን ለማዘመን ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት የመሟላት ስራዎች እንደተከናወነ፤ የካፒታል ኢንቨስትመንት ስራዎችን በማጠናከር የድርጅቱን የሎጀስቲክስ አቅም ለመገንባት 5 የደረቅ ጭነት ተሳቢ ፣ 6 የመስክና 7 የከተማ ተሸከርካሪዎች ግዢ ተከናውኖ ወደ ስራ እንዲገቡ እንደተደረገ አመልክተዋል፡፡ 
በተጨማሪም 500 ኩንታል የመጫን አቅም ያላቸው 24 ተሳቢ የደረቅ ጭነት ተሸከርካሪዎች ግዢ የተካሄደ ሲሆን የተለያዩ ውጪያዊ ችግሮችን ቢኖሩም በቀጣዩ ሶስት ወራት ውስጥ ርክክብ የካሄዳል ተብሎ እንደሚጠበቅና በአጠቃላይ ከ230 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገ አመልክተዋል፡፡
በማጠቃለያም የድርጅቱ ሠራተኖች እየተከናወኑ ያሉትን የለውጥ ስራዎችና የተገኙትን ውጤቶች እንዲሁም የታቀዱትን ዓበይት ተግባራት ግምት ውስጥ በማስገባት የድርጅቱ አመራሮችና ሠራተኞች ሙሉ አቅማቸውንና ዕወቀታቸውን ድርጅቱን ለማሳደግ እንዲያውሉ የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አሳስበዋል፡፡

Image3