ኢኢግልድ በስትራቴጂክ ዕቅዱና በአሰራር መመሪያዎች ረቂቅ ላይ ሲያካሂድ የነበረውን ግምገማ አጠናቀቀ

13/05/2024

ኢኢግልድ ስትራቴጂክ ዕቅዱና ሌሎችም የአሰራር ስርዓቶቹን እየገመገመ ይገኛል

10/05/2024

ኢኢግልድ በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ላይ ተሳተፈ

09/05/2024

ኢኢግልድ 10ኛው አገር ዓቀፍ የሕብረት ሥራ ማሕበራት ኤግዚቢሽንና ባዛር ተሳተፈ

15/02/2024

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በኢኢግልድ ጉብኝት አካሄዱ

29/01/2024

የአመራሮችና የባለሙያዎች ቅንጅትና የስራ ትጋት ለድርጅቱን አፈጻጸም ውጤታማነት ሚና እንደሚኖረው ተገለጸ

17/01/2024

ማስታወቂያ

27/11/2023

የምግብ ዘይት በቫይታሚን ለማበልጸግ የሚያስፈልገውን የፕሪሚክስ አቅርቦትን አስመልክቶ የወጣ ማስታወቂያ

06/11/2023

ኢኢግልድ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ገመገመ

06/11/2023

ማስታወቂያ

25/10/2023

ኢኢግልድ የ4.2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አበረከተ

17/10/2023

ኢኢግልድ የ16.5 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት በተመጣጣኝ ዋጋ አቀረበ

14/09/2023

ኢኢግልድ የዲስትሪክቶችን የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የቀጣይ ዓመት ዕቅድ ግምገማ አካሄደ

23/08/2023

የኢኢግልድ ሥራ አመራር ቦርድ አባላት በግንባታ ላይ የሚገኙና ግንባታቸው የተጠናቀቁ ፕሮክቶችን ጎበኙ

31/07/2023

ኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኞች የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አካሄዱ

27/07/2023

የኢኢግልድ ሴት ሠራተኞች ፎረም ተመሰረተ

20/07/2023

ኢኢግልድ የ2015 በጀት ዓመት የስምንት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ

11/04/2023

ኢኢግልድ ለ33 የድርጅቱ ባለሙያዎች የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ልማትና ትግበራ ስልጠና ሠጠ

23/03/2023

ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ ፕሮጀክቶች ግንባታ ገብኝት ተካሄደ

18/01/2023

አርአያነት ያለው ተግባር

14/09/2022

— 20 Items per Page
Showing 1 - 20 of 38 results.

የኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኞች የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ በላቀ ሁኔታ ለመፈጸም ዝግጁ መሆናቸውን አስታወቁ

ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የዲስትሪክት ሃላፊዎችና ፈጻሚዎች የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድን በላቀ ውጤት ለማስመዝገብ የሚጠበቅባቸውን ሃለፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ፡፡

ይህ የተገለጸው የድርጅቱ የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም፣ የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድና በጸደቁ የድርጅቱ አራት የሥራ መመሪያዎች ላይ የማዕከላዊ፣ የምዕራብ፣ የምስራቅና ፣የሰሜንና የደቡብ ዲስትሪክቶች ሃላፊዎችና አመራሮች በተሳተፉበት ከነሐሴ 21-22 እንዲሁም ከነሐሴ 28-29ቀን 2014 ዓ.ም በሐዋሳ፣ ጅማ እና ቢሾፍቱ እና ባህር ዳር ከተሞች ባካሄዱት የምክክር መድረክ ላይ ነው፡፡

በተካሄዱት የውይይት መድረኮች የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ የሺመቤት ነጋሽ በተለይ በሐዋሳ መድረክ ላይ እንደገለጹት በውይይት መድረኩ አመራሮች እና ፈጻሚዎች በአፈጻጸም ሂደት የነበሯቸውን ሚና፣ ጥንካሬዎቻቸውንና ክፍተቶቻቸውን የገመገሙበትና ጠንካራ ጎኖቻቸውን አጠናክረው ለመቀጠል የጋራ መግባባት የተደረሰበት መድረክ እንደሆነ እንዲሁም የታዩ ክፍተቶች ታርመው በ2015 በጀት ዓመት ታላላቅ ዕቅዶችን ለማሳካት ሁሉም የድርሻውን በጋራ እና በተቀናጀ መልኩ የድርጅቱን ተልዕኮ ለማሳካት የጋራ ስምምነት የተደረሰበት መድረክ እንደሆነ አመልክተዋል፡፡

በተያያዘም የድርጅቱ የኢንዱስትሪ ውጤቶች ግዢና ሽያጭ ዘርፍ ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰለሞን ግርሻ በጅማ ከተማ በተካሄደው መድረክ የበላይ አመራሮች የዲስትሪክት ሃላፊዎችና ፈጻሚዎች በግንባር ተገናኝተው በ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና በ2015 ዕቅድ እንዲሁም በተሻሻሉ መመሪያዎች ላይ መወያየታቸው እንደ ትልቅ የንግድ ድርጅት እየተካሄዱ ያሉትን የሪፎርም ሥራዎች በአግባቡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው፡፡ በተጨማሪም የ2015 በጀት ዓመት ዕቅዶችን በውጤታማነት ለመተግበር የዚህ ዓይነት መድረኮች የራሱ ሚና ያለው እንዳለው ያብራሩት አቶ ሰለሞን ቀደም ሲል ከነበረው ልማዳዊ አሠራርና አካሄድ ተወጥቶ እንደድርጅት የምንታደስበትን ጎዳና የምንይዝበት መድረክ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

በምክክር መድረኮቹ የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ በዝርዝር ቀርቦ ውይይት የተካሄዶበታል፡፡ በተጨማሪም በአፈጻጸም ሂደት እንቅፋት የነበሩ የስራ መመሪያዎች ከወቅቱ የድርጅቱ ነባራዊ ሁኔታ ጋር እንዲጣጣሙ ተደርገው የጸደቁ የስራ መመሪያዎች፤ የዲስትሪክት ሃላፊዎችና የሽያጭ ባለሙያዎች በተሳተፉባቸው መድረኮች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡ በመድረኮቹ የግዢ፣ የሽያጭ የፋይናንስ እና የንብረት አወጋገድ መመሪያዎች ቀርበው ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራዎች ተከናውኗል፡፡

በማጠቃለያም በውይይት መድረኮቹ ተሳታፊ የነበሩ የድርጅቱ የበላይና መካከለኛ አመራሮች፣ የዲስትሪክት ሃላፊዎች፣ የቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድን በላቀ ውጤት ለማስመዝገብ የሚጠበቅባቸውን ሃለፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡