ኢኢግልድ የአቢሲኒያ ኢንዱስትሪዎች ሽልማት ከፍተኛ ተሸላሚ ሆነ
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅትና የኢትዮጵያ ፖስታ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሠነድ ተፈራረሙ
23/10/2024
በኢንዱስትሪ ግብዓቶች አቅርቦት ተግዳሮቶችና መፍትሄ ላይ ውይይት ተካሄደ
14/10/2024
እንኳን ደስ አላችሁ!!!
11/10/2024
ኢኢግልድ ላገኘው የ2016 በጀት ዓመት ስኬታማ አፈጻጸም ለአመራሮቹና ሠራተኞቹ እውቅና ሰጠ
26/08/2024
ኢኢግልድ የአቢሲኒያ ኢንዱስትሪዎች ሽልማት ከፍተኛ ተሸላሚ ሆነ
22/07/2024
የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታ አስተዳደርና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሃላፊዎች የችግኝ ተከላ አካሄዱ
20/07/2024
የማዕከላዊና የምዕራብ ዲስትሪክት ጽ/ቤቶች አስር ወራት ዕቅድ አፈጻጸምና 2017 የኮርፖሬት ዕቅድ ግምገማ ተካሄደ
20/05/2024
ኢኢግልድ በስትራቴጂክ ዕቅዱና በአሰራር መመሪያዎች ረቂቅ ላይ ሲያካሂድ የነበረውን ግምገማ አጠናቀቀ
13/05/2024
ኢኢግልድ ስትራቴጂክ ዕቅዱና ሌሎችም የአሰራር ስርዓቶቹን እየገመገመ ይገኛል
10/05/2024
ኢኢግልድ በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ላይ ተሳተፈ
09/05/2024
ኢኢግልድ 10ኛው አገር ዓቀፍ የሕብረት ሥራ ማሕበራት ኤግዚቢሽንና ባዛር ተሳተፈ
15/02/2024
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በኢኢግልድ ጉብኝት አካሄዱ
29/01/2024
የአመራሮችና የባለሙያዎች ቅንጅትና የስራ ትጋት ለድርጅቱን አፈጻጸም ውጤታማነት ሚና እንደሚኖረው ተገለጸ
17/01/2024
ማስታወቂያ
27/11/2023
የምግብ ዘይት በቫይታሚን ለማበልጸግ የሚያስፈልገውን የፕሪሚክስ አቅርቦትን አስመልክቶ የወጣ ማስታወቂያ
06/11/2023
ኢኢግልድ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ገመገመ
06/11/2023
ማስታወቂያ
25/10/2023
ኢኢግልድ የ4.2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አበረከተ
17/10/2023
ኢኢግልድ የ16.5 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት በተመጣጣኝ ዋጋ አቀረበ
14/09/2023
ኢኢግልድ የዲስትሪክቶችን የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የቀጣይ ዓመት ዕቅድ ግምገማ አካሄደ
23/08/2023
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የአቢሲኒያ የሽልማት ድርጅት በኢንዱስትሪ ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ኢንዱስትሪዎች፣ ድርጅቶችና ኩባንያዎች ለመሸለም ሐምሌ 14 ቀን 2016 ዓ.ም በኢንተር ላግዠሪ ሆቴል በተዘጋጀው የእውቅና ስነ ስርዓት ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ በወርቅ ደረጃ ተሸላሚ ሆነ፡፡
በዝግጅቱ የዕለቱ የክብር እንግዳ፣ የቀድሞ የኢፌዲሪ ፕሬዘዳንትና የአቢሲኒያ ሽልማት ድርጅት የበላይ ጠባቂ ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ሽልማቱን ሰጥተዋል፡፡
ሽልማቱን የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ የሺመቤት ነጋሽ የተረከቡ ሲሆን ድርጅቱ በኢንዱስትሪ ግብዓቶችና ውጤቶች አቅርቦትና ስርጭት ለዓመታት በሰጠው አገልግሎት እንዲሁም ጥራትንና ደንበኞችን ማዕከል በማድረግ ላከናወናቸው ተግባራት ሽልማቱ እንደተሰጠው ተገልጿል፡፡
በሽልማቱ ሥነ ስርዓት ላይ የኢኢግልድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ድርጅቱን ውጤታማ ለማድረግ በሰጡት ጠንካራ አመራር የወርቅ ሜዳልያ፣ ኒሻንና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል፡፡ በተያያዘም ለ12 መካከለኛ አመራሮች፣ የቅርንጫፍ ሃላፊዎችና ቡድን መሪዎች ሜዳልያና ሰርተፍኬት የተሰጠ ሲሆን እንደተቋም በወርቅ ደረጃ ድርጅቱ ዋንጫና ሰርተፍኬት ተሸላሚ ሆኗል፡፡
በዚህ የሽልማት ስነ ስርዓት 33 ኢንዱስትሪዎች፣ ድርጅቶችና ኩባንያዎች እንዲሁም ድርጅቶቹን ለዚህ ያበቁ አመራሮችና ባለሙያዎቻቸው ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ደርጅት የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን ከአገር ውስጥና ከውጭ አገር በመግዛት ማቅረብና በሂደትም በአገር ውስጥና በውጭ አገር የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን በማምረት ለማቅረብ የተቋቋመ የመንግስት የልማት ድርጅት ነው፡፡