በግብዓት አቅርቦት ፓሊሲ፣ ስትራቴጅዎች እና ሌሎች ሰነዶች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
የኢኢግልድ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ውጤታማ መሆኑ ተገለጸ
20/10/2025
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ ሆነ
10/10/2025
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የአመራሮች ስልጠና በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ተካሔደ
25/09/2025
የኢኢግልድ የክር ማጠንጠኞ ማዕከል ሰራተኞች በፋብሪካዎች ተገኝተው የመስክ ጉብኝት አካሄዱ
23/09/2025
የኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኞች የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅና የሠራተኞችን ዓመታዊ በዓል አከበሩ
09/09/2025
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት (ኢግልድ) በበጀት ዓመቱ ጠንካራ አፈጻጸም አስመዘገበ
27/08/2025
Financial and Audit Report 2021/22
12/05/2025
በአገራዊና ተቋማዊ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ተካሔደ
21/04/2025
የኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኞች ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀንን አከበሩ
17/03/2025
የኢኢግልድ ሽያጭ ቅርንጫፎችና ዲስትሪክቶች የስምንት ወራት አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ
17/03/2025
በግብዓት አቅርቦት ፓሊሲ፣ ስትራቴጅዎች እና ሌሎች ሰነዶች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
11/03/2025
Financial and Audit Report 2020/21
28/01/2025
ማስታወቂያ
25/10/2023
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የበላይ አመራሮች ከኢኢግልድ አመራሮች ጋር ውይይትና የስራ ጉብኝት አካሄዱ
26/12/2024
የኢኢግልድ የበላይ አመራሮችና ሃላፊዎች በግንባታ ላይ የሚገኘውን ዋና መ/ቤት ህንፃ ጎበኙ
02/12/2024
ኢኢግልድ በበጀት ዓመቱ አራት ወራት የዕቅዱን 96 በመቶ ማከናወኑ ተገለጸ
23/10/2024
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅትና የኢትዮጵያ ፖስታ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሠነድ ተፈራረሙ
23/10/2024
በኢንዱስትሪ ግብዓቶች አቅርቦት ተግዳሮቶችና መፍትሄ ላይ ውይይት ተካሄደ
14/10/2024
እንኳን ደስ አላችሁ!!!
11/10/2024
ኢኢግልድ ላገኘው የ2016 በጀት ዓመት ስኬታማ አፈጻጸም ለአመራሮቹና ሠራተኞቹ እውቅና ሰጠ
26/08/2024
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት(ኢኢግልድ) ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት በኢንዱስትሪ ግብዓቶች አቅርቦት ጋር በተያያዘ የአምራች ኢንዱሰትሪውን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በተዘጋጀ ፖሊሲ፣ በተቀረፁ የተለያዩ ጥናቶችና ስትራቴጂዎች ላይ ከየካቲት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት በቢሾፍቱ ከተማ ለኢኢግልድ ከፍተኛ አመራሮች፣ ከተለያየ ክፍል ለተውጣጡ ዳይሬክተሮች፣ የዲሰተሪክት ሃላፊዎችና ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
በስልጠናው የኢኢግልድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ የሺመቤት ነጋሽ የመክፈቻ ንግግር በማድረግ ስልጠናውን ያስጀመሩ ሲሆን የስልጠናው ዋና ዓላማ ኢኢግልድ ከኢንዱስትሪዎች ፍላጎት አንጻር የግብዓት አቅርቦት ስራ ሂደቱን ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ስትራቴጂ ጋር የተናበበና የተቀናጀ በማድረግ ለመስራት እና የግብዓት አቅርቦት ሰንሰለቱን የተሳለጠ በማድረግ በቀጣይ ውጤታማ ስራ ለመስራት እንዲያስቻል ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን አመልክተዋል፡፡
ለሁለት ቀናት በተካሄደው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የተለያዩ ስትራቴጂዎችና ጥናቶች የቀረቡ ሲሆን የኢትዮጲያ የኢንዱስትሪ ፖሊሲ፣ የተኪ ምርት ስትራቴጂ፤ የአምራች ኢንዱስትሪ የትስስር ስትራቴጅ ሰነድ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የኤክስፖርት ስትራቴጂ፣ የቆዳ ስትራቴጂና የማስፈጸሚያ ስልት እንዲሁም የጥጥ ግብይት ስርዓት ጥናቶች ለስልጠናው ተሳታፊዎች ቀርበዋል፡፡ በቀረቡት ሰነድ ላይም የስልጠናው ተሳታፊዎች ከኢኢግልድ አንፃር ጥያቄዎችን እና አስተያየቶችን በማቅረብ ሰፋ ያለ ውይይት በኢንዱሰትሪ ሚኒሰቴር የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ዋና ዳይሬክተር በሆኑት ዶ/ር ሚልኬሳ ጃግሜ እና በአሰልጣኞች አወያይነት ተካሂዷል፡፡
በመጨረሻም የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሚልኬሳ ጃግሜ በስልጠናውና የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐግብር ማጠናቀቂያ ላይ እንደገለጹት የዚህ ዓይነት የስልጠና መድረክ በኢንዱስትሪ ግብዓት አቅርቦት ዘርፍ ዋና ባለድርሻ ለሆኑት የኢኢግልድ ከፍተኛ፣ መካከለኛ አመራሮችና ባለሙያዎች መዘጋጀቱ የኢንዱስትሪ ግብዓት አቅርቦት ሰንሰለቱን የተሳለጠ እንደሚያደርገው አመልክተው፤ የዚህ ዓይነት ይዘት ያላቸው የተለያዩ ነገር ግን የአንድ ዓላማ ግብን ለማሳከት የሚያስችሉ፤ ተቋማትን የሚያስተሳስሩ ስትራቴጂዎችና ጥናቶች ላይ የጋራ ግንዛቤ መያዝ በእጅጉ አስፈላጊ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡





