የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ብር 265 ሚሊዮን የተጣራ ትርፍ ማግኘቱ ተገለጸ

ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ ፕሮጀክቶች ግንባታ ገብኝት ተካሄደ
18/01/2023

አርአያነት ያለው ተግባር
14/09/2022

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የፍጆታ ምርቶች መሸጫ ዋጋ
09/09/2022

የኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኞች የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ በላቀ ሁኔታ ለመፈጸም ዝግጁ መሆናቸውን አስታወቁ
29/08/2022

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት አመራሮችና ሠራተኞች ለአቅመ ደካሞች የቤት ዕድሳት የማስጀመር እና የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ አከናወኑ
07/08/2022

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት በ9ኛው ሀገር አቀፍ የህብረት ስራ ኤግዚቢሽንና ባዛር ላይ በመሳተፍ ምርትና አገልግሎቱን አስተዋወቀ
11/02/2022

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ብር 265 ሚሊዮን የተጣራ ትርፍ ማግኘቱ ተገለጸ
04/02/2022

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት አመራሮችና ሠራተኞች ለአቅመ ደካሞች የቤት ዕድሳት የማስጀመር እና የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ አከናወኑ
12/08/2022

በአዮዲን ያልበለጸገ ጥሬ ጨው ለምግብነት የሚያቀርቡ አካላት ከህገወጥ ተግባራቸው እንዲታቀቡ ጥሪ ቀረበ::
02/09/2021

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያ አምስት ወራት አፈጻጸሙን ገመገመ::
02/09/2021

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት 2 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ድጋፍ ለሃገር መከላከያ ሠራዊት ሰጠ::
02/09/2021

የኢኢግልድ አመራሮች በወረኢሉ ግንባር በመገኘት ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ አበረከቱ::
02/09/2021

ኢኢግልድ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ
02/09/2021

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት አመራሮችና ሠራተኞች ነጩ ፖስታ ለነጩ ቤተመንግስት መርሃ ግብርን አካሄዱ
02/09/2021

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ የግንባታ የስምምነት ውል ተፈራረመ፡፡
02/09/2021

ከውጪ አገር ከተገዛው ዘይት 5.8 ሚሊየን ሊትር መግባቱ ተገለፀ።
02/09/2021

ኢኢግልድ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የ2 ሚሊዮን ብር ድጋፍና የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ አመራሮችና ሠራተኞች እውቅናና ሽልማት ሰጠ::
02/09/2021

ኢኢግልድ ለመንግስትና የግል ድርጅቶች ሠራተኞች የስንዴ ዱቄት በተመጣጣኝ ዋጋ አቀረበ
02/09/2021

ኢኢግልድ በየወሩ 52,080 ኩንታል የኢንዱስትሪ ጨው ለቆዳ ፋብሪካዎች ለማቅረብ የግዢ ውል ተፈራረመ
02/09/2021

ኢኢግልድ ከ2.7 ቢሊዮን ብር በላይ የኢንዱስትሪ ግብዓቶችና ውጤቶችን አቀረበ
02/09/2021
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት በ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወራት አፈጻጸም ብር 265 ሚሊዮን የተጣራ ትርፍ ማግኘቱ ተገለጸ፡፡
ይህ የተገለጸው ድርጅቱ የ2014 በጀት ዓመት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸሙንና የቀጣዩን ስድስት ወራት ዕቅድ የድርጅቱ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ እና አባላት፣ የድርጅቱ የበላይና መካከለኛ አመራሮችና የድርጅቱ ሠራተኞች በተገኙበት ጥር 28 እና 29 / 2014 ዓ.ም በቢሾፍቱ ባዘጋጀው የግምገማና የምክክር መድረክ ላይ ነው፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የድርጅቱ ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተካ ገ/የስ እንደገለጹት ድርጅቱ ከነበረበት አሰከፊ ችግሮች ወጥቶ የሪፎርም ሥራዎችን በማከናወን ለትርፋማነት መድረሱ፤ የድርጅቱ ሠራተኞችና አመራሮች ጥምር ውጤት ሲሆን ይህንን ውጤት አጠናክሮ በመቀጠል ኢኢግልድ በቀጣይም የተሸለ ውጤት ለማስመዝገብ በቁርጠኝነት መስራት ይገባል፡፡
አያይዘውም በድርጅቱ የተሻለ አደረጃጀትና የአሰራር ሥርዓት ለመዘርጋት ከተደረገው የእስካሁኑ ጥረት በተጨማሪ በቀጣይም ጊዜያት የተጀመረሩትን የሪፎርም ሥራዎች በማጠናከር ወደላቀ ደረጃ ከፍ ለማድረግ የአመራሩና የሰራተኞች ተቀነቀጅቶ መስራት ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ የሺመቤት ነጋሽ እንደገለጹት የድርጅቱ አመራሮችና የዲስትሪክትና የሽያጭ ቅርንጫፍ ሃላፊዎች ድርጅቱን ወደተሸለ ደረጃ ለማሻገር የተጀመሩትን የሪፎርም ስራዎች በማስቀጠል በተጠናከረ መንገድ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ለመግባት ከወዲሁ በቁርጠኝነት ሊሰሩ ይገባል፡፡
አያይዘውም የድርጅቱ የበላይ አመራር የአሰራር ክፍተቶችን በመሙላት ድርጅቱን ወደተሻለ ደረጃ የሚያሻግር አሰራሮን የመተግበር ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አመልክተዋል፡፡
ለሁለት ቀናት በተካሄደው በዚሁ የግምገማና የምክክር መድረክ የድርጅቱ የ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት አፈጻጸም ሪፖርትና የቀሪዎቹ ስድስት ወራት እቅድ በስትራቴጂክ እቅድ ዝግጅትና ግምገማ ዳይሩክቶሬት ቀርቦ በጥልቀት ግምገማና ውይይት ተካሂዶበታል፡፡