የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት 2 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ድጋፍ ለሃገር መከላከያ ሠራዊት ሰጠ::

EIIDE offered 16.5 million liters of edible oil at a reasonable price
14/09/2023

EIIDE conducted an evaluation of the of the 2022/23 fiscal year plan and the next year's plan of the enterprise
23/08/2023

Members of the Management Board visited projects of EIIDE
31/07/2023

Managers and Employees of EIIDE Conducted Green Legacy
27/07/2023

EIIDE has launched a women's workers forum
20/07/2023

ኢኢግልድ የ2015 በጀት ዓመት የስምንት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ
11/04/2023

ኢኢግልድ ለ33 የድርጅቱ ባለሙያዎች የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት ልማትና ትግበራ ስልጠና ሠጠ
23/03/2023

ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ ፕሮጀክቶች ግንባታ ገብኝት ተካሄደ
18/01/2023

አርአያነት ያለው ተግባር
14/09/2022

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የፍጆታ ምርቶች መሸጫ ዋጋ
09/09/2022

የኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኞች የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ በላቀ ሁኔታ ለመፈጸም ዝግጁ መሆናቸውን አስታወቁ
29/08/2022

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት አመራሮችና ሠራተኞች ለአቅመ ደካሞች የቤት ዕድሳት የማስጀመር እና የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ አከናወኑ
07/08/2022

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት በ9ኛው ሀገር አቀፍ የህብረት ስራ ኤግዚቢሽንና ባዛር ላይ በመሳተፍ ምርትና አገልግሎቱን አስተዋወቀ
09/02/2022

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ብር 265 ሚሊዮን የተጣራ ትርፍ ማግኘቱ ተገለጸ
07/02/2022

በአዮዲን ያልበለጸገ ጥሬ ጨው ለምግብነት የሚያቀርቡ አካላት ከህገወጥ ተግባራቸው እንዲታቀቡ ጥሪ ቀረበ
30/12/2021

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት አመራሮችና ሠራተኞች ለአቅመ ደካሞች የቤት ዕድሳት የማስጀመር እና የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ አከናወኑ
12/08/2022

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት 2 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ድጋፍ ለሃገር መከላከያ ሠራዊት ሰጠ::
02/09/2021

የኢኢግልድ አመራሮች በወረኢሉ ግንባር በመገኘት ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ አበረከቱ::
02/09/2021

ኢኢግልድ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ
02/09/2021

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት አመራሮችና ሠራተኞች ነጩ ፖስታ ለነጩ ቤተመንግስት መርሃ ግብርን አካሄዱ
02/09/2021
የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት አመራሮች 2 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ደረቅ ራሽንና ቁሳቁሶችን ህዳር 26 ቀን 2014 ዓ.ም በደብረ ብርሃን ከተማ በመገኘት ለሃገር መከላከያ ሠራዊት አስረከቡ፡፡
የኢኢግልድ ዋና ስራ አሰፈጻሚ ክብርት ወ/ሮ የሺመቤት ነጋሽ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት እንደገለጹት ድርጅቱ ባለፉት ዓመታት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት እና በተለያየዩ ጊዜያት በተፈጠሩ ማህበራዊ ቀወሶች 15 ሚሊዮን ብር የሚደርስ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን የአሁኑን ድጋፍ የተለየ የሚደርገው ከዚህ በፊት ተደረገውን ድጋፍ ሳይጨምር የድርጅቱ አመራሮችና ሠራተኞች የአንድ ወር ደሞዛቸውን በመልቀቅ ብር 5.5 ሚሊዮን የሚጠጋ ድጋፍ ማበርከታቸው እንደሆነ አመልክተዋል፡፡
አያይዘውም ከድርጅቱ አመራሮችና ሠራተኞች ከተሰጠው ድጋፍ ውስጥ ባለፈው ሣምንት በወረኢሉ ግንባር በአካል በመገኘት 1.6 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ደረቅ ራሽንና ቁሳቁሶች የበረከቱ እንደሆነ ገልጸው በአሁኑ ወቅትም በደብረብርሃን ከተማ በአካል በመገኘት 2 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ድጋፎችን ለሠራዊቱ ማቅረባቸውን አብራርተዋል፡፡
በማጠቃለያቸውም በአገራችን የጦርነት ታሪክ ባንዳዎች በተለያዩ ጊዜያት እንደነበሩ ነገር ግን ሁልጊዜም እንደሚያፍሩና ኢትዮጵያም እንደምታሸንፍ አመልክተዋል፡፡
የግንባሩ ኮማንድ ፖስት ዋና አስተባባሪና የመከላከያ ሚኒስቴር ተወካይ ድጋፉን በተረከቡበት ወቅት እንደገለጹት ከራስ በፊት ህዝብና ሀገር ማስጠበቅን ዓላማ በማድረግ እየሠራ የሚገኘው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ኢትዮጵያን ለማዋረድና ለማፍረስ የመጣውን ጁንታ በማርበድበድ ላይ የሚገኝ ሲሆን ሠራዊቱም ይህንን ዓላማውን ለማስፈጸም የሚተማመነው ደጀን ህዝብ ደግሞ ሃብት በማሰባሰብና በአካልም ሆነ በተለያየ መልክ የሚያደርገው ድጋፍ ለሠራዊቱ ከፍተኛ አቅምና ጉልበት እንዲሁም የድል መነሻና መዳረሻ ሆኗቸዋል፡፡
ይህንንም ህዝባዊ ድጋፍ መሠረት በማድረግ በወረራ የተያዙትን ስፍራዎች በማስለቀቅ ተጨማሪ ድሎችን ለማብሰር የመከላከያ ሠራዊቱ ሌት ተቀን እየሰራ እንደሚገኝም የኮማንድ ፖስቱ ዋና አስተባባሪ አመልክተዋል፡፡
የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት በአገሪቱ ባሉት ከ80 በላይ ቅርንጫፎች ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ግብዓት የሚያቀርብና የኢንዱስትሪ ውጤቶችና መሠረታዊ ሸቀጦች የሚያሰራጭ የመንግስት የልማት ድርጅት ሲሆን በአሁኑ ወቅት ጁንታው እያካሄደ በሚገኘው ጥቃት 12 የሽያጭ ቅርንጨፎቹ ሙሉ በሙሉ በመዘረፋቸው ከ500 ሚሊዮን ብር በለ ኪሳራ ደርሶበታል፡፡