ድርጅቱ ተልዕኮውን በተሟላ ሁኔታ ለማሳካትና በገበያ ውስጥ ተወዳዳሪነቱን ለማጠናከር የጀመራቸውን ጥረቶች አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ተገለፀ።
ድርጅቱ ተልዕኮውን በተሟላ ሁኔታ ለማሳካትና በገበያ ውስጥ ተወዳዳሪነቱን ለማጠናከር የጀመራቸውን ጥረቶች አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ተገለፀ።
16/03/2026
Financial and Audit Report 2023/24
25/03/2026
Financial and Audit Report 2022/23
25/03/2026
ኢኢግልድ የ2018 በጀት ዓመት 8 ወራት አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ
16/03/2026
ሙያን መሠረት አድርጎ የሚሰጥ ተከታታይ ስልጠና ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለጸ
09/03/2026
በስድስት ወራት አፈጻጸም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ዲስትሪክቶችና ቅርንጫፎች ዕውቅና ተሰጠ
27/01/2026
በመንግሥት የልማት ድርጀቶች የግዢ አፈጻጸም መመሪያና በለውጥ ሥራዎች ላይ ሲሰጥ የነበረዉ ሥልጠና ተጠናቀቀ
10/11/2025
የኢኢግልድ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ውጤታማ መሆኑ ተገለጸ
20/10/2025
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ ሆነ
10/10/2025
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የአመራሮች ስልጠና በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ተካሔደ
25/09/2025
የኢኢግልድ የክር ማጠንጠኞ ማዕከል ሰራተኞች በፋብሪካዎች ተገኝተው የመስክ ጉብኝት አካሄዱ
23/09/2025
የኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኞች የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅና የሠራተኞችን ዓመታዊ በዓል አከበሩ
09/09/2025
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት (ኢግልድ) በበጀት ዓመቱ ጠንካራ አፈጻጸም አስመዘገበ
27/08/2025
Financial and Audit Report 2021/22
12/05/2025
በአገራዊና ተቋማዊ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ተካሔደ
21/04/2025
የኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኞች ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀንን አከበሩ
17/03/2025
የኢኢግልድ ሽያጭ ቅርንጫፎችና ዲስትሪክቶች የስምንት ወራት አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ
17/03/2025
በግብዓት አቅርቦት ፓሊሲ፣ ስትራቴጅዎች እና ሌሎች ሰነዶች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
11/03/2025
Financial and Audit Report 2020/21
28/01/2025
ማስታወቂያ
25/10/2023
ይህ የተገለፀው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (ኢኢግልድ) የ2018 በጀት አመት የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በገመገመበት ወቅት ነው።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ መለሰ መና እንደገለጹት፣ የተቋሙ የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ግልጽ፣ ተዓማኒ እና የአመራር ቅንጅት የታየበት ነው።ተቋሙ ቀደም ሲል በከባድ ችግር ውስጥ እንደነበር ጠቅሰው፣ የአመራር ለውጥ በማድረግ ከዚያ ሁኔታ መውጣቱንና አሁን በተሻለ ሁኔታ እየሠራ መሆኑን ገልፀዋል።ተቋሙ የኦዲት ግኝቶችን በየጊዜው ማረም፣ በዓለም የሚኖረውን ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን በመቋቋም ሽያጭና ትርፍን ማስቀጠል፣ አዳዲስ ደንበኞችን ማምጣት እና የገበያ ተደራሽነትን በሚዲያ መሣሪያዎች ማሳደግ እንደ ጠንካራ አፈፃፀሞች ተጠቁመዋል።
እንዲሁም በግዥና ሽያጭ ሂደቶች ጥራትን ማረጋገጥ፣ የሴቶች የአመራር ተሳትፎን ማሳደግ እና የሰው ሀብት ልማት ሥርዓቱን ማጠናከር ተቋሙን ለሌሎች ድርጅቶች አርአያ የሚያደርገው መሆኑን ገልፀዋል። በተጨማሪም የISO 9001:2015 የጥራት አስተዳደር ሥርዓት ለመተግበር የተደረጉ ዝግጅቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል።
ድርጅቱን በቀጣይ የሀብት አስተዳደርን ማሻሻል፣ የቅርንጫፍ ቢሮዎችን ማዘመን እና የዲጂታል ስርዓት ለማስፋት የተጀመሩ ሥራዎች እንዲጠናከሩ አሳስበዋል።የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ ኢንጅነር ስለሺ ኮሬ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ተቋሙ ከቋሚ ኮሚቴው ጋር ይበልጥ በመተባበር ለለውጥ የሚሠራ መሆኑን ገልፀው፣ ችግሮችን በጥናት፣ በዘላቂነትና በአስተማማኝ መልኩ ከሥር መሠረቱ ለመፍታት በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ያስጠናቸው ጥናቶች ጥሩ መሆናቸውን ገልፀዋል። ይህንን ጥናት በማስተባበርና በማረጋገጥ ወደ ሥራ መግባት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በግዥ፣ በሽያጭና በተደራሽነት ዘርፎች የተቋሙ እቅዶችና አፈጻጸሞች የተሻሻሉ መሆናቸውን፣ ከኦዲት ጋር ተያይዞ የነበሩ ችግሮችም በተገቢ መንገድ መፍታታቸውን ገልፀው፤ ተቋሙን ለመለወጥ እና ሀብት ለማፍራት የሚደረጉ ጥረቶች አበረታች መሆናቸውን ጠቅሰው፣ ይህንኑ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።ገበያውንና ወቅቱን በማየት የድርጅቱን ሕንጻ ዲዛይን በመቀየር ሙሉ በሙሉ ወደ ቢሮ አገልግሎት ለመለወጥ የተደረጉ ጥረቶች አበረታች መሆናቸውን እና ቀሪ የግንባታ ሥራዎችን በፍጥነት ማጠናቀቅ እንደሚገባም አስረድተዋል።
በቀጣይ የድርጅቱን ይዞታ ማስከበር፣ የኢንዱስትሪ ጨው ግብዓት አቅርቦት አማራጮችን ማስፋት ትኩረት ሊደረግባቸው ይገባል ብለዋል።የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ዳዊት አዳነ በበኩላቸው፤ ድርጅቱ ብቃት ባለው የሰው ኃይልና በቴክኖሎጂ የተደገፈ የአሰራር ሥርዓት፣ ጠንካራ የአቅርቦትና የግብይት ሰንሰለት በመገንባት፣ ጥራታቸውን የጠበቁ የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን በማልማትና በማቅረብ እንዲሁም የተመረጡ የኢንዱስትሪ ውጤቶችን ለተጠቃሚዎች በማድረስ፣ የሀገሪቱ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ውጤታማነት እንዲጨምር እና የገበያ መረጋጋት እንዲፈጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል።
ተቋሙ በ2018 በጀት ዓመት 9 ወራት እቅድ አፈፃፀሙ በኢንዱስትሪ ግብዓቶች እና ውጤቶች ግዥ እና ሽያጭ የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገቡን ጠቁመው፣ ተቋሙ በበጀት አመቱ 580 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን ለቋሚ ኮሚቴው ተናግረዋል።በበጀት ዓመቱ ለኢንዱስትሪ ጨው አቅርቦት አፈፃፀም ዝቅተኛ መሆን ምክንያት የነበሩ ጉዳዮችን በቀጣይ በመፍታት የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ ጥረት የሚደረግ መሆኑን ገልፀዋል፡፡





