Financial and Audit Report 2023/24

25/03/2026

Financial and Audit Report 2022/23

25/03/2026

ኢኢግልድ የ2018 በጀት ዓመት 8 ወራት አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ

16/03/2026

ሙያን መሠረት አድርጎ የሚሰጥ ተከታታይ ስልጠና ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለጸ

09/03/2026

በስድስት ወራት አፈጻጸም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ዲስትሪክቶችና ቅርንጫፎች ዕውቅና ተሰጠ

27/01/2026

በመንግሥት የልማት ድርጀቶች የግዢ አፈጻጸም መመሪያና በለውጥ ሥራዎች ላይ ሲሰጥ የነበረዉ ሥልጠና ተጠናቀቀ

10/11/2025

የኢኢግልድ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ውጤታማ መሆኑ ተገለጸ

20/10/2025

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ ሆነ

10/10/2025

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የአመራሮች ስልጠና በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ተካሔደ

25/09/2025

የኢኢግልድ የክር ማጠንጠኞ ማዕከል ሰራተኞች በፋብሪካዎች ተገኝተው የመስክ ጉብኝት አካሄዱ

23/09/2025

የኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኞች የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅና የሠራተኞችን ዓመታዊ በዓል አከበሩ

09/09/2025

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት (ኢግልድ) በበጀት ዓመቱ ጠንካራ አፈጻጸም አስመዘገበ

27/08/2025

Financial and Audit Report 2021/22

12/05/2025

በአገራዊና ተቋማዊ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ተካሔደ

21/04/2025

የኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኞች ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀንን አከበሩ

17/03/2025

የኢኢግልድ ሽያጭ ቅርንጫፎችና ዲስትሪክቶች የስምንት ወራት አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ

17/03/2025

በግብዓት አቅርቦት ፓሊሲ፣ ስትራቴጅዎች እና ሌሎች ሰነዶች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

11/03/2025

Financial and Audit Report 2020/21

28/01/2025

ማስታወቂያ

25/10/2023

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የበላይ አመራሮች ከኢኢግልድ አመራሮች ጋር ውይይትና የስራ ጉብኝት አካሄዱ

26/12/2024

— 20 Items per Page
Showing 1 - 20 of 66 results.

ሙያን መሠረት አድርጎ የሚሰጥ ተከታታይ ስልጠና ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለጸ

የአሠራር ክፍተቶችን መሠረት አደርጎ የሚሰጥ ተከታታይ ሥልጠና በአፈጻጸም ወቅት ሊፈጠሩ የሚችሉ ችግሮችን በማስወገድ ስራዎችን እንደሚያሳልጥ ኢኢግልድ በአዳማ ከተማ ለሁለት ቀናት ባዘጋጀው ስልጠና የተሳተፉ የድርጅቱ ባለሙያዎች ገለጹ::

ይህ የተገለጸው የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ከየካቲት 28-29/2018 ዓ.ም በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በድርጅቱ በስራ ላይ ካዋለው የኢንተርፕራይዝ ሐብት እቅድ/ አስተዳደር (ERP) ትግበራ ጋር በተያያዘ ባዘጋጀው የሁለት ቀናት ሥልጠና እየተሳተፉ የሚገኙ የፋይናንስና የሽያጭ ባለሙያዎች ናቸው፡፡

በሥልጠናው የተሳተፉ ባለሙያዎች በአፈጻጸም ወቅት የገጠሟቸው ችግሮችና የአሠራር ክፍቶችን አቅርበው በድርጅቱ የተተገበረውን የኢንተርፕራይዝ ሐብት እቅድ(ERP) ካለሙት ባለሙያ ሙያዊ ማብራሪና ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፡፡

በተጨማሪም በስልጠናው የተሳተፉ በቡድን ተከፍው በተዘጋጁት አራት የስልጠና ማዕከላት ውስጥ ተግባራዊ ልምምድና ሙያዊ ድጋፍ እንዲሰጣቸው ተደርጓል፡፡

ሥልጠናው በዋናነት በግዢ ጥያቄ አቀረቀረብ፣ ለሸቀጥ በሚቆረጡ ደረሰኞች አዘገጃጀት፣ በኢንቨንተሪ ማስተላለፍና ማረጋገጨዎች፣ሽያጭና ገቢን ማስታረቅ፣ የባንክ ወጪና ገቢን ማስታረቅ እና በሌሎችም ተመሳሳይ ከኢንተርፕራይዝ ሐብት እቅድ/ አስተዳደር (ERP) ጋር የተያያዙ የአሰራር ሥርዓቶች ላይ በማተኮር በተግባር የተደገፈ ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡

በሥልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ የኢኢግልድ ተ/የዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ዮናስ ዘለቀ ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር ድርጅቱ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ኢ አር ፒ ተግብሮ እየሰራ ያለ እንደሆነና በዚህም ሥራ በውስጥና በውጭ ኦዲተሮች ሒሳቡ እየተረጋገጠ እንደሆነ አመልክተው በኦዲት ሪፖርቶች ላይ የሚነሱ የተለያዩ የአሰራር ችግሮችን በተለይም የአመዘጋገብና የሶፍት ዌር አጠቃቀም ክፍተቶችን መነሻ በማድረግ በተጨማሪም ድርጅቱ እየተገበረ ያለውን ነባሩን ኢ አር ፒ ሲስተም ቨርዥን በሁሉም ቅርንጫፎችና ዲስትሪክት ጽ/ቤቶች የማሳደግ ስራ ጋር በተያያዘ ስልጠናው እንደተዘጋጀ አመልክተዋል፡፡

በዚህም መሠረት የአይ ቲ እና ካሸሮችን ጨምሮ በዋና መስሪያ ቤትና ዲስትሪክት ያሉ የፋይናንስ ባለሙያዎችን በተፈጠሩ የአጠቃቀም ችግሮችና የአሰራር ስህተቶች ላይ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና እንደተሰጠ ገልጸው በስልጠናው የተካፈሉት የሽያጭ ቅርንጫፎችና የዲስትሪክት ባለሙያዎች ባለፉት ጊዜያት የታዩትን የአሰራር ስህተቶች ደግመው ሊሰሩ እንደማይገባ አጽንኦት በመስጠት ለስራቸው ትኩረት ሠጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ ማሳሰቢያና የስራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡