ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ ፕሮጀክቶች ግንባታ ገብኝት ተካሄደ
በመንግሥት የልማት ድርጀቶች የግዢ አፈጻጸም መመሪያና በለውጥ ሥራዎች ላይ ሲሰጥ የነበረዉ ሥልጠና ተጠናቀቀ
10/11/2025
የኢኢግልድ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ውጤታማ መሆኑ ተገለጸ
20/10/2025
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ ሆነ
10/10/2025
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የአመራሮች ስልጠና በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ተካሔደ
25/09/2025
የኢኢግልድ የክር ማጠንጠኞ ማዕከል ሰራተኞች በፋብሪካዎች ተገኝተው የመስክ ጉብኝት አካሄዱ
23/09/2025
የኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኞች የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅና የሠራተኞችን ዓመታዊ በዓል አከበሩ
09/09/2025
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት (ኢግልድ) በበጀት ዓመቱ ጠንካራ አፈጻጸም አስመዘገበ
27/08/2025
Financial and Audit Report 2021/22
12/05/2025
በአገራዊና ተቋማዊ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ተካሔደ
21/04/2025
የኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኞች ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀንን አከበሩ
17/03/2025
የኢኢግልድ ሽያጭ ቅርንጫፎችና ዲስትሪክቶች የስምንት ወራት አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ
17/03/2025
በግብዓት አቅርቦት ፓሊሲ፣ ስትራቴጅዎች እና ሌሎች ሰነዶች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
11/03/2025
Financial and Audit Report 2020/21
28/01/2025
ማስታወቂያ
25/10/2023
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የበላይ አመራሮች ከኢኢግልድ አመራሮች ጋር ውይይትና የስራ ጉብኝት አካሄዱ
26/12/2024
የኢኢግልድ የበላይ አመራሮችና ሃላፊዎች በግንባታ ላይ የሚገኘውን ዋና መ/ቤት ህንፃ ጎበኙ
02/12/2024
ኢኢግልድ በበጀት ዓመቱ አራት ወራት የዕቅዱን 96 በመቶ ማከናወኑ ተገለጸ
23/10/2024
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅትና የኢትዮጵያ ፖስታ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሠነድ ተፈራረሙ
23/10/2024
በኢንዱስትሪ ግብዓቶች አቅርቦት ተግዳሮቶችና መፍትሄ ላይ ውይይት ተካሄደ
14/10/2024
እንኳን ደስ አላችሁ!!!
11/10/2024
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት(ኢኢግልድ) አመራሮችና ሠራተኞች ድርጅቱ በ2 ቢሊዮን ብር እያስገነባ ያለው የዋና መ/ቤት ህንጻና ግንባታቸው የተጠናቀቁ 48 ለንግድ ሥራ የሚያገለግሉ ሱቆች ጉብኝት ጥር 9 ቀን 2015 ዓ.ም አካሄዱ፡፡
በአገራችን የተካሄደውን ለውጥ ተከትሎ ኢኢግልድ ውስጥ የሚታዩትን የአሰራርና አፈጻጸም እንዲሁም የመልካም አስተዳደርና የሙስና ችግሮች ለመፍታት በተወሰደው እርምጃ የአመራሮች ለውጥ በማካሄድና የተለያዩ የሪፎርም ሥራዎች በማከናወን ላይ የሚገኙ ሲሆን ከዚሁ ጋር በተያያዘ በተጨባጭ ውጤት የተገኘባቸው ሁለት ፕሮጀክቶች ተመርጠው በድርጅቱ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም ሠራተኞች እንዲጎበኙ ተደርገዋል፡፡
ድርጅቱ ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ መድቦ እያስገነባ የሚገኘው ባለ 18 ፎቅ የዋና መ/ቤት ህንጻ አንዱ ሲሆን ህንጻው ከዋና መ/ቤት ጽ/ቤት ባሻገር የተለያዩ አገልግሎት የሚሰጡ በተለይም ለባንክ፣ ሱፐር ከርኬት፣ ለጂምና ለተለያዩ አገልግሎቶች ሊውል ታቅዶ ግንባታው እተካሄደ እንደሆነ በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል፡፡
ከሜክሲኮ አደባባይ ዝቅ ብሎ አፍሪካ ፍብረት አካባቢ እየተገነባ የሚገኘው ይህ ህንጻ በሁለት ዓመታት ውስጥ የሚጠናቀቅ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የፕሮጀክቱ 46 በመቶ እንደተከናወነ እስከ 2015 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ የግንባታው 80 በመቶ እንደሚጠናቀቅ፤ ፕሮጀክቱ በዕቅዱ መሠረት እየተካሄደ እንደሚገኝ የፕሮጀክቱ አማካሪ ድርጅት አመልክቷል፡፡
በአመራሮችና ሠራተኞች ጉብኝት የተካሄደበት ሌላው ፕሮጀክት ግንባታቸው የተጠናቀቁና ለአገልግሎት ዝግጁ የተደረጉት በቃሊቲ ማዕከላዊ ዲስትሪክት የሚገኙት 48 ሱቆች ሲሆኑ ከዚህም በተጨማሪ ለቆዳ ውጤቶች ማምረቻ እንዲያገለግሉ የተገነቡትም ሼዶች በዚሁ ወቅት ጉብኝት ተካተዋል፡፡
በቀጣይም ድርጅቱ በቆዳ ውጤቶች ላይ በማተኮር በቃሊቲ ማዕከላዊ ዲስትሪክት ባለ 4 ፎቅ ህንጻዎችን ለመገንባትና በቆዳ ውጤቶች ኤክስፖርት ንግድ ላይ ለመሰማራት እየሰራ እንደሚገኝም በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል፡፡
የኢኢግል ድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ የሺመቤት ነጋሽ በጉብኝቱ ማጠቃለያ ላይ እንደገለጹት ድርጅቱ የነበሩበትን የመልካም አስተዳደር ፣ የሙስና፣ ወቅቱን የዋጀ ዘመናዊ የአሰራርና የአፈጻጸም ችግሮች በመለየት የሪፎርም ስራዎች ተጠናክሮ እንዲሰራ በመደረጉ አሁን ለተገኙት ውጤቶች አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን አመልክተዋል፡፡
በተካሄዱትም የሪፎርም ስራዎች ድርጅቱን የሚመጥን መዋቅር በማስጠናት እንዲተገበር የተደረገ መሆኑን የገለጹት ወ/ሮ የሺመቤት ቀድሞ የነበሩ መመሪያዎች እንዲሻሻሉና 10 አዳዲስ መመሪያዎች ተዘጋጅተው በድርጅቱ ስራ አመራር ቦርድ እንዲጸድቁ ተደርገው ወደስራ እንደተገባ፤ አሰራርን ለማዘመን ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት የመሟላት ስራዎች እንደተከናወነ፤ የካፒታል ኢንቨስትመንት ስራዎችን በማጠናከር የድርጅቱን የሎጀስቲክስ አቅም ለመገንባት 5 የደረቅ ጭነት ተሳቢ ፣ 6 የመስክና 7 የከተማ ተሸከርካሪዎች ግዢ ተከናውኖ ወደ ስራ እንዲገቡ እንደተደረገ አመልክተዋል፡፡
በተጨማሪም 500 ኩንታል የመጫን አቅም ያላቸው 24 ተሳቢ የደረቅ ጭነት ተሸከርካሪዎች ግዢ የተካሄደ ሲሆን የተለያዩ ውጪያዊ ችግሮችን ቢኖሩም በቀጣዩ ሶስት ወራት ውስጥ ርክክብ የካሄዳል ተብሎ እንደሚጠበቅና በአጠቃላይ ከ230 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገ አመልክተዋል፡፡
በማጠቃለያም የድርጅቱ ሠራተኖች እየተከናወኑ ያሉትን የለውጥ ስራዎችና የተገኙትን ውጤቶች እንዲሁም የታቀዱትን ዓበይት ተግባራት ግምት ውስጥ በማስገባት የድርጅቱ አመራሮችና ሠራተኞች ሙሉ አቅማቸውንና ዕወቀታቸውን ድርጅቱን ለማሳደግ እንዲያውሉ የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አሳስበዋል፡፡



