ኢኢግልድ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የ2 ሚሊዮን ብር ድጋፍና የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ አመራሮችና ሠራተኞች እውቅናና ሽልማት ሰጠ::

በግብዓት አቅርቦት ፓሊሲ፣ ስትራቴጅዎች እና ሌሎች ሰነዶች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
11/03/2025

Financial and Audit Report 2020/21
28/01/2025

ማስታወቂያ
25/10/2023

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የበላይ አመራሮች ከኢኢግልድ አመራሮች ጋር ውይይትና የስራ ጉብኝት አካሄዱ
26/12/2024

የኢኢግልድ የበላይ አመራሮችና ሃላፊዎች በግንባታ ላይ የሚገኘውን ዋና መ/ቤት ህንፃ ጎበኙ
02/12/2024

ኢኢግልድ በበጀት ዓመቱ አራት ወራት የዕቅዱን 96 በመቶ ማከናወኑ ተገለጸ
23/10/2024

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅትና የኢትዮጵያ ፖስታ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሠነድ ተፈራረሙ
23/10/2024

በኢንዱስትሪ ግብዓቶች አቅርቦት ተግዳሮቶችና መፍትሄ ላይ ውይይት ተካሄደ
14/10/2024

እንኳን ደስ አላችሁ!!!
11/10/2024

ኢኢግልድ ላገኘው የ2016 በጀት ዓመት ስኬታማ አፈጻጸም ለአመራሮቹና ሠራተኞቹ እውቅና ሰጠ
26/08/2024

ኢኢግልድ የአቢሲኒያ ኢንዱስትሪዎች ሽልማት ከፍተኛ ተሸላሚ ሆነ
22/07/2024

የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታ አስተዳደርና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሃላፊዎች የችግኝ ተከላ አካሄዱ
20/07/2024

የማዕከላዊና የምዕራብ ዲስትሪክት ጽ/ቤቶች አስር ወራት ዕቅድ አፈጻጸምና 2017 የኮርፖሬት ዕቅድ ግምገማ ተካሄደ
20/05/2024

ኢኢግልድ በስትራቴጂክ ዕቅዱና በአሰራር መመሪያዎች ረቂቅ ላይ ሲያካሂድ የነበረውን ግምገማ አጠናቀቀ
13/05/2024

ኢኢግልድ ስትራቴጂክ ዕቅዱና ሌሎችም የአሰራር ስርዓቶቹን እየገመገመ ይገኛል
10/05/2024

ኢኢግልድ በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ላይ ተሳተፈ
09/05/2024

ኢኢግልድ 10ኛው አገር ዓቀፍ የሕብረት ሥራ ማሕበራት ኤግዚቢሽንና ባዛር ተሳተፈ
15/02/2024

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በኢኢግልድ ጉብኝት አካሄዱ
29/01/2024

የአመራሮችና የባለሙያዎች ቅንጅትና የስራ ትጋት ለድርጅቱን አፈጻጸም ውጤታማነት ሚና እንደሚኖረው ተገለጸ
17/01/2024

ማስታወቂያ
27/11/2023
ኢኢግልድ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የ2 ሚሊዮን ብር ድጋፍና የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ አመራሮችና ሠራተኞች እውቅናና ሽልማት ሰጠ
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት(ኢኢግልድ) እየተካሄደ ያለውን የሀገር ህልውናን የማዳን ዘመቻ መነሻ በማድረግ ሀገር ለመከላከያ ሠራዊት የ2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ እና ድርጅቱ በ2013 በጀት ዓመት ያስመዘገበውን አጥጋቢ ውጤት ምክንያት በማድረግ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የድርጅቱ አመራሮችና ሠራተኞች እውቅናና ሽልማት ነሐሴ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ሰጠ፡፡
ለሠራዊታችን ድጋፉ የተሰጠው ኢኢግልድ በ2013 በጀት ዓመት ያስመዘገበውን የላቀ አፈጻጸም ምክንያት በማድረግ በድርጅቱ ቅጥር ጊቢ አጥጋቢ ውጤት ላስመዘገቡ አመራሮችና ሠራተኞች ዕውቅናና ሽልማት ለመስጠት ባዘጋጀው መርሃ ግብር ላይ ሲሆን በሥነሥርዓቱም ላይ የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ክብርት ወ/ሮ የሺመቤት ነጋሽ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ተወካይ አስረክበዋል፡፡
በድጋፍ አሰጣጡ ስነስርዓት ላይ ከሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የመከላከያ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ ብ/ጄነራል አስረስ አያሌው እእንደገለጹት ከሀገራችን የቅርብ፣ የሩቅ የውስጥ ጠላቶች ጋር በማበር ሀገር ለማፈራረስ እየሰራ የሚገኘው ፀረ-ህዝብ ቡድን ለማስወገድ ሠራዊቱ ቀን ከሌሊት እየተዋደቀ የሚገኝ ሲሆን በተለይ ይህ ህገ ወጥ ቡድን በአማራና አፋር በአጎራባች ስፍራዎች ጥቃቱን ለማስፋፋት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመግታት በሰራዊቱ የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ የኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኖች ከሠጡት የቁሳቁስ ድጋፍ በተጨማሪ አሁን በገንዘብ ተደረገው የ2 ሚሊየን ብር ድጋፍና በድርጅቱ ከሚሰሩ ሠራተኞች መካከል በፈቃደኝነት ለመዝመት መነሳሳታቸው ለሰራዊቱ ተጨማሪ ስንቅ እንደሚሆነው ሃላፊው አመልክተዋል፡፡
በተያያዘም በዋናነት ድርጅቱ የ2013 በጀት ዓመት ያስመዘገበውን የላቀ ውጤት መነሻ በማድረግ ባካሄደው የእውቅናና የሽልማት መርሃግብር የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መላኩ አለበል፣ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታና የኢኢግልድ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ተካ ገ/የስ እንዲሁም የተከበሩ ወ/ሮ መሠረት አባተ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ኢንዱስትሪ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና የኢኢግልድ የስራ አመራር ቦርድ አባላት ተገኝተዋል፡፡
የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በዕውቅናና ሽልማት ስነስርት ላይ አገራችን በሪፎርም ውስጥ እንደምትገኝ አመልክተው በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ፣ በመከላከያ እና በሌሎችም ዘርፎች እተካሄደ ያለው ሪፎርም ውጤት እያስመዘገበ እንደሆነና በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ውስጥ እየተካሄደ ያለው የሪፎርም ሥራ በተለይም በአመራር፣ በአሰራር፣ በቴክኖሎጂ እና በዲጂታል አውቶሜሽን ስራዎች የሚያበረታቱና ድርጅቱ በበጀት ዓመቱ ላስመዘገበው ውጤት አስዋጽኦ እንዳላቸው አመልክተዋል፡፡
ኢኢግልድ ባለፉት ዓመታት የነበሩበትን የተወሳሰቡ ችግሮች በአብዛኛው እንደተወጣና በተካሄዱትም የለውጥ ስራዎች ድርጅቱን ከውድቀት በመታደግ በ2013 በጀት ዓመት የተገኘው ውጤት የሚያበረታታና በቀጣዩም ዓመት የተሸለ ውጤቶችን ለማስመዝገብ ከፍተኛ ርብርብ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡
የኢኢግልድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ክብርት ወ/ሮ የሺመቤት ነጋሽ በስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ድርጅቱ ባለፉት ዓመታት ካለፈባቸው የተወሳሰቡ የአሰራር፣ የአደረጃጀት፣ የግብዓት፣ የብልሹ አሰራር፣የቡድንተኝነት፣ የአሰራር እና አሳተፊነት ችግሮች ተወጥቶ አሁን የሚገኝበት ደረጃ ለመድረስ እልህ አስጨራሽ ችግሮች እንዳጋጠሟቸው በዝርዝር አመልክተው የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የድርጅቱ የስራ አመራር ቦርድ እና የድርጅቱ አመራሮች ስትራቴጂክ ውሳኔዎችን በመወሰን በአሁኑ ወቅት ችግሩን ተወጥተው በ2013 በጀት ዓመት በድርጅቱ ታሪክ ተገኝቶ የማይታወቀውን 96.7 በመቶ እቅድ አፈጻጸም እንደተመዘገበ አመልክተዋል፡፡
በመጨረሻም በዚህ ዓመት የተገኘውን ውጤት ምክንያት በማድረግ ይህንን ውጤት ላስመዘገቡና ለተገኘውም ውጤት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ የበላይ ሃላፊዎች፣የስራ አመራር ቦርድ አባላት፣የኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኞች፣ እጅግ ባነሰ ደሞዝ ድርጅቱን ድርጅቴ ብለው 25 እና ከዚያ በላይ ላገለገሉ ሠራተኞች እንዲሁም በክብር በጡረታ ለተገለሉ ሠራተኞች ይህ የእውቅና መርሃግብር እንደተዘጋጀ ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት በአገራችን የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች ያለባቸውን የግብዓት አቅርቦት ችግር ለመፍታት በዋናነት በኢንዱስትሪ ግብዓት አቅርቦት ስራ ላይ ተሰማራ የመንግስት የልማት ድርጅት ነው፡፡