በግብዓት አቅርቦት ፓሊሲ፣ ስትራቴጅዎች እና ሌሎች ሰነዶች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

11/03/2025

Financial and Audit Report 2020/21

28/01/2025

ማስታወቂያ

25/10/2023

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የበላይ አመራሮች ከኢኢግልድ አመራሮች ጋር ውይይትና የስራ ጉብኝት አካሄዱ

26/12/2024

የኢኢግልድ የበላይ አመራሮችና ሃላፊዎች በግንባታ ላይ የሚገኘውን ዋና መ/ቤት ህንፃ ጎበኙ

02/12/2024

ኢኢግልድ በበጀት ዓመቱ አራት ወራት የዕቅዱን 96 በመቶ ማከናወኑ ተገለጸ

23/10/2024

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅትና የኢትዮጵያ ፖስታ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሠነድ ተፈራረሙ

23/10/2024

በኢንዱስትሪ ግብዓቶች አቅርቦት ተግዳሮቶችና መፍትሄ ላይ ውይይት ተካሄደ

14/10/2024

እንኳን ደስ አላችሁ!!!

11/10/2024

ኢኢግልድ ላገኘው የ2016 በጀት ዓመት ስኬታማ አፈጻጸም ለአመራሮቹና ሠራተኞቹ እውቅና ሰጠ

26/08/2024

ኢኢግልድ የአቢሲኒያ ኢንዱስትሪዎች ሽልማት ከፍተኛ ተሸላሚ ሆነ

22/07/2024

የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታ አስተዳደርና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሃላፊዎች የችግኝ ተከላ አካሄዱ

20/07/2024

የማዕከላዊና የምዕራብ ዲስትሪክት ጽ/ቤቶች አስር ወራት ዕቅድ አፈጻጸምና 2017 የኮርፖሬት ዕቅድ ግምገማ ተካሄደ

20/05/2024

ኢኢግልድ በስትራቴጂክ ዕቅዱና በአሰራር መመሪያዎች ረቂቅ ላይ ሲያካሂድ የነበረውን ግምገማ አጠናቀቀ

13/05/2024

ኢኢግልድ ስትራቴጂክ ዕቅዱና ሌሎችም የአሰራር ስርዓቶቹን እየገመገመ ይገኛል

10/05/2024

ኢኢግልድ በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ላይ ተሳተፈ

09/05/2024

ኢኢግልድ 10ኛው አገር ዓቀፍ የሕብረት ሥራ ማሕበራት ኤግዚቢሽንና ባዛር ተሳተፈ

15/02/2024

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በኢኢግልድ ጉብኝት አካሄዱ

29/01/2024

የአመራሮችና የባለሙያዎች ቅንጅትና የስራ ትጋት ለድርጅቱን አፈጻጸም ውጤታማነት ሚና እንደሚኖረው ተገለጸ

17/01/2024

ማስታወቂያ

27/11/2023

— 20 Items per Page
Showing 1 - 20 of 50 results.

ኢኢግልድ በየወሩ 52,080 ኩንታል የኢንዱስትሪ ጨው ለቆዳ ፋብሪካዎች ለማቅረብ የግዢ ውል ተፈራረመ

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ለቆዳ ኢንዱስትሪዎች በግብዓትነት የሚያገለግል 52,080 ኩንታል የኢንዱሰትሪ ጨው በግዢ በየወሩ ለማቅረብ በአፋር ክልል ከሚገኝ አፍዴራ የጨው አምራቾች የህብረት ስራ ማህበር ጋር የስምምነት ውል ሚያዚያ 11 ቀን 2013 ዓ.ም ተፈራረመ፡፡ 


የውል ስምምነቱ መሠረት ኢኢግልድ ከአፍዴራ ጨው አምራቾች የህብረት ስራ ማህበር በየወሩ 52,080 ኩንታል በመግዛት ስምምነት ላይ የደረሰና ለተጠቃሚ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ እየሠራ ይገኛል፡፡
ለዚህም ተፈጻሚነት እንዲረዳ ትራንስፖርተሮችን በማመቻቸት ስራዎች እየተከናወኑ እንደሆነና ለዘንድሮውም የትንሠኤ በዓልና የረመዳን በዓል በሚፈጸም እርድ ቆዳ እንደይባክንና እንዳይጣል አስቸኳይ ግዢ በመፈጸም ጨው ወደ ገበያው እንዲገባ ተደርጓል፡፡


ከውል ስምምነት መፈራረም በኋላ 1,680 ኩንታል ጨው ተጓጉዞ በድርጅታችን የቃሊቲ የሽያጭ ቅርንጫፍ መጋዘን ተራግፏል፡፡


በተጨማሪም በግዢ ሂደት ላይ የሚገኘው ጨው የድርጅታችን እና የጨው አምራቹ የህብረት ስራ ማህበር ስምና ሎጎ ጎን ለጎን በሚታተምበት ማሸጊያ የሚታሸግ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ለምግብነትም እንዳይውል በጨዉ ላይ ኬሚካል እንደተጨመርበትና ይህም በማሸጊያው ላይ መገለጹ ተብራርቷል፡፡ 
በተያያዘም ድርጅታችን በየወሩ 52,080 ኩንታል በመግዛት ለተጠቃሚ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ትራንስፖርተሮችን በማመቻቸት የተሰራ ቢሆንም የኢንዱስትሪ ጨውን ለማቅረብ የተስማማው የአምራቾች ማህበር በታቀደው መጠን ድርጅታችን ባቀረባቸው የትራንስፖርት ተሸከርካሪዎችና የጨው ማሸጊያ ከረጢት መጠን በሚፈለገው ፍጥነት ያለማከናወን ክፍተቶች እንደሆነ ታውቋል፡፡ በተለይም አምራች ማህበራቱ በቂ የሰው ሃይል አሰማርቶ ስራውን ያለማከናወንና ምርቱን ለማቅረብ በቂ ዝግጅት አለማድረግ በዋናነት የታዩ ችግሮች እንደሆኑም ተገልጿል፡፡


በመሆኑም የታየውን የአሰራር ክፍተት በመረዳት የኢኢግልድ ከፍተኛና መካከለኛ አመራርሮች ከአፋር ክልል ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ አመራሮችና ጨውን ለማምረት ስምምነት ከገባው አፍዴራ የጨው አምራቾች ሃላ/የተ የግል ማህበር አመራሮች ጋር በታዩት ችግሮች ዙሪያ በመወያየት ለመፍታት በስፍራው ይገኛሉ፡፡ 
ኢኢግልድ ለአምራች ኢንዱስትሪዎቻችን ግብዓት በማቅረብ በዘርፉ የሚታየውን የኢንዱስትሪ ግብዓቶች እጥረት ክፍተት ለመሙላት የተቋቋመ የመንግስት የልማት ድርጅት ነው፡፡