ኢኢግልድ ለመንግስትና የግል ድርጅቶች ሠራተኞች የስንዴ ዱቄት በተመጣጣኝ ዋጋ አቀረበ
Financial and Audit Report 2023/24
25/03/2026
Financial and Audit Report 2022/23
25/03/2026
ኢኢግልድ የ2018 በጀት ዓመት 8 ወራት አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ
16/03/2026
ሙያን መሠረት አድርጎ የሚሰጥ ተከታታይ ስልጠና ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለጸ
09/03/2026
በስድስት ወራት አፈጻጸም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ዲስትሪክቶችና ቅርንጫፎች ዕውቅና ተሰጠ
27/01/2026
በመንግሥት የልማት ድርጀቶች የግዢ አፈጻጸም መመሪያና በለውጥ ሥራዎች ላይ ሲሰጥ የነበረዉ ሥልጠና ተጠናቀቀ
10/11/2025
የኢኢግልድ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ውጤታማ መሆኑ ተገለጸ
20/10/2025
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ ሆነ
10/10/2025
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የአመራሮች ስልጠና በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ተካሔደ
25/09/2025
የኢኢግልድ የክር ማጠንጠኞ ማዕከል ሰራተኞች በፋብሪካዎች ተገኝተው የመስክ ጉብኝት አካሄዱ
23/09/2025
የኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኞች የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅና የሠራተኞችን ዓመታዊ በዓል አከበሩ
09/09/2025
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት (ኢግልድ) በበጀት ዓመቱ ጠንካራ አፈጻጸም አስመዘገበ
27/08/2025
Financial and Audit Report 2021/22
12/05/2025
በአገራዊና ተቋማዊ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ተካሔደ
21/04/2025
የኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኞች ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀንን አከበሩ
17/03/2025
የኢኢግልድ ሽያጭ ቅርንጫፎችና ዲስትሪክቶች የስምንት ወራት አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ
17/03/2025
በግብዓት አቅርቦት ፓሊሲ፣ ስትራቴጅዎች እና ሌሎች ሰነዶች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
11/03/2025
Financial and Audit Report 2020/21
28/01/2025
ማስታወቂያ
25/10/2023
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የበላይ አመራሮች ከኢኢግልድ አመራሮች ጋር ውይይትና የስራ ጉብኝት አካሄዱ
26/12/2024
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት በገበያው ላይ የሚታየውን የሸቀጦች ዋጋ ንረትና የአቅርቦት ችግር ለማርገብ በመሠረታዊ የምግብ ምርቶች ላይ እየሰራ እንደሚገኝና በተለይም የስንዴ ዱቄትና የምግብ ዘይት በተመጣጣኝ ዋጋ እያሰራጨ እንደሚገኝ የድርጅቱ ሽያጭ ዘርፍ ሚያዚያ 13 ቀን 2013 አስታወቀ፡፡
የድርጅቱ ሽያጭ ዘርፍ እንዳስታወቀው ኢኢግልድ ከአድአ ዱቄት ፋብሪካ ባለ 50፣ 25 እና 10 ኪሎ ግራም 1ኛ ደረጃ የስንዴ ዱቄት ተረክቦ በመጋዘኑ እንዲገባ ያደረገ ሲሆን በያዝነው ሳምንት በአዲስ አበባና በዙሪያዋ በሚገኙ ከተሞች በሚገኙ የድርጅቱ ቅርንጫፎች ምርቱን ለማሰራጨትና በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል፡፡
በተያያዘም በአዲስ አበባ ከሶማሌ ተራ፣ በርበሬ ተራና ጨው በረንዳ ቅርንጫፎች በስተቀር በስምንት የድርጅቱ ቅርንጫፎች ለህብረተሰቡ የስንዴ ዱቄት ሽያጭ ይከናወናል፡፡
በተጨማሪም በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የመንግስትና የግል ድርጅቶች የሰራተኞቻቸውን ዝርዝር በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ደብዳቤያቸውን በማቅረብ ግዢ መፈጸም እንደሚችሉ ተገልጷል፡፡
ባለፉት ሶስት ወራት በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ በርካታ የመንግስትና የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ባለ 5 ሊትር ፈሳሽ የምግብ ዘይት በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ህብረተሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን መደረጉ ይታወሳል፡፡
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት በአገራችን በተለይም በመሠረታዊ ሸቀጦች ላይ የሚታየውን የዋጋ ንረት ለማርገብና የአቅርቦት ችግር ለመቅረፍ እየሠራ የሚገኝ የመንግስት የልማት ድርጅት ነው፡፡