በመንግሥት የልማት ድርጀቶች የግዢ አፈጻጸም መመሪያና በለውጥ ሥራዎች ላይ ሲሰጥ የነበረዉ ሥልጠና ተጠናቀቀ

10/11/2025

የኢኢግልድ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ውጤታማ መሆኑ ተገለጸ

20/10/2025

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ ሆነ

10/10/2025

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የአመራሮች ስልጠና በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ተካሔደ

25/09/2025

የኢኢግልድ የክር ማጠንጠኞ ማዕከል ሰራተኞች በፋብሪካዎች ተገኝተው የመስክ ጉብኝት አካሄዱ

23/09/2025

የኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኞች የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅና የሠራተኞችን ዓመታዊ በዓል አከበሩ

09/09/2025

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት (ኢግልድ) በበጀት ዓመቱ ጠንካራ አፈጻጸም አስመዘገበ

27/08/2025

Financial and Audit Report 2021/22

12/05/2025

በአገራዊና ተቋማዊ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ተካሔደ

21/04/2025

የኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኞች ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀንን አከበሩ

17/03/2025

የኢኢግልድ ሽያጭ ቅርንጫፎችና ዲስትሪክቶች የስምንት ወራት አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ

17/03/2025

በግብዓት አቅርቦት ፓሊሲ፣ ስትራቴጅዎች እና ሌሎች ሰነዶች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

11/03/2025

Financial and Audit Report 2020/21

28/01/2025

ማስታወቂያ

25/10/2023

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የበላይ አመራሮች ከኢኢግልድ አመራሮች ጋር ውይይትና የስራ ጉብኝት አካሄዱ

26/12/2024

የኢኢግልድ የበላይ አመራሮችና ሃላፊዎች በግንባታ ላይ የሚገኘውን ዋና መ/ቤት ህንፃ ጎበኙ

02/12/2024

ኢኢግልድ በበጀት ዓመቱ አራት ወራት የዕቅዱን 96 በመቶ ማከናወኑ ተገለጸ

23/10/2024

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅትና የኢትዮጵያ ፖስታ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሠነድ ተፈራረሙ

23/10/2024

በኢንዱስትሪ ግብዓቶች አቅርቦት ተግዳሮቶችና መፍትሄ ላይ ውይይት ተካሄደ

14/10/2024

እንኳን ደስ አላችሁ!!!

11/10/2024

— 20 Items per Page
Showing 1 - 20 of 61 results.

በመንግሥት የልማት ድርጀቶች የግዢ አፈጻጸም መመሪያና በለውጥ ሥራዎች ላይ ሲሰጥ የነበረዉ ሥልጠና ተጠናቀቀ

ለኢኢግልድ አመራሮችና ባለሙያዎች በመንግሥት የልማት ድርጀቶች የግዢ አፈጻጸም መመሪያና በለውጥ ሥራዎች በተለይም በከይዘንና በቢ ኤስ ሲ ላይ እንዲሁም በአዎንታዊ አመለካከት ላይ ለሁለት ቀናት በቢሾፍቱ ከተማ ሲሰጥ የነበረው ሥልጠና ተጠናቋል።

በሁለተኛው ቀን የስልጠና መርሃ ግብር አቶ ዳዊት አዳነ የኢኢግልድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ተወካይ በከይዘን፣ አቶ መህዲ ዑመር የለውጥ ሥራዎች ባለሙያ በቢ ኤስ ሲ(BSC) ትግበራ እና ወ/ሮ ዉድነሸ ክፍሌ የስነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ዳይሬክተር ከጸረ-ሙስና አሰራር ሥርዓት ጋር በተያያዘ ሥልጠና ሰጥተዋል፡፡

በሥልጠናው የተሳተፉ አመራሮችና ባለሙያዎች እንደገለፁት ለሁለት ቀናት የተሰጡት ሥልጠናዎች በሥራቸው ላይ ለሚጠበቀው ለውጥ፣ መሻሻልና ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው አመልክተው በድርጅቱ አፈጻጸም ውጤት የሚያመጡ የሥራ ዘርፎች ላይ ሥልጠናዎች ተዘጋጅተው ለሚመለከታቸው አመራሮችና ባለሙያዎች ቀጣይነት ባለው መልኩ አንዲሰጥ አስተያየታቸውን አቅርበዋል።

በሥልጠናው ማጠቃለያ ላይ የኢኢግልድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተወካይ አቶ ዳዊት አዳነ ድርጅቱ ገንዘብና ጊዜ መድቦ የዚህ ዓይነት ሥልጠና ለአመራሮችና ባለሙያዎች ሲያዘጋጅ፤ ከሥልጠናው የሚጠብቀው ውጤት እንዳለ አመልክተው የዚህ ሥልጠና ተሳታፊዎች በተመደቡበት የሥራ መስክ የሚጠበቅባቸውን ውጤት ማምጣትና የተቋሙን ተልእኮ ለማሳካት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል ።