ኢኢግልድ የደንበኞች ግንኙነት/አገልግሎት አስተዳደር ሥርዓት አስጠንቶ ወደ ትግበራ ገባ
ኢኢግልድ የደንበኞች ግንኙነት/አገልግሎት አስተዳደር ሥርዓት አስጠንቶ ወደ ትግበራ ገባ
04/10/2026
አቶ ዳዊት አዳነ የኢኢግልድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተመደቡ
29/09/2026
ኢኢግልድ የትምህርት መሣሪያዎች ድጋፍና የመማሪያ ክፍሎችን ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ አስቀመጠ
11/08/2026
ለኢኢግልድ ሠራተኞች በሙሉ Duplicate 2
21/05/2026
ለኢኢግልድ ሠራተኞች በሙሉ
21/05/2026
ድርጅቱ ተልዕኮውን በተሟላ ሁኔታ ለማሳካትና በገበያ ውስጥ ተወዳዳሪነቱን ለማጠናከር የጀመራቸውን ጥረቶች አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ተገለፀ።
16/03/2026
Financial and Audit Report 2023/24
25/03/2026
Financial and Audit Report 2022/23
25/03/2026
ኢኢግልድ የ2018 በጀት ዓመት 8 ወራት አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ
16/03/2026
ሙያን መሠረት አድርጎ የሚሰጥ ተከታታይ ስልጠና ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለጸ
09/03/2026
በስድስት ወራት አፈጻጸም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ዲስትሪክቶችና ቅርንጫፎች ዕውቅና ተሰጠ
27/01/2026
በመንግሥት የልማት ድርጀቶች የግዢ አፈጻጸም መመሪያና በለውጥ ሥራዎች ላይ ሲሰጥ የነበረዉ ሥልጠና ተጠናቀቀ
10/11/2025
የኢኢግልድ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ውጤታማ መሆኑ ተገለጸ
20/10/2025
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ ሆነ
10/10/2025
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የአመራሮች ስልጠና በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ተካሔደ
25/09/2025
የኢኢግልድ የክር ማጠንጠኞ ማዕከል ሰራተኞች በፋብሪካዎች ተገኝተው የመስክ ጉብኝት አካሄዱ
23/09/2025
የኢኢግልድ አመራሮችና ሠራተኞች የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅና የሠራተኞችን ዓመታዊ በዓል አከበሩ
09/09/2025
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት (ኢግልድ) በበጀት ዓመቱ ጠንካራ አፈጻጸም አስመዘገበ
27/08/2025
Financial and Audit Report 2021/22
12/05/2025
በአገራዊና ተቋማዊ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ተካሔደ
21/04/2025
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለማሳለጥ የሚያስችል የደንበኞች ግንኙነት/አገልግሎት/ አስተዳደር ሥርዓት/Customer's Relations management System/ አስጠንቶ በስራ ላይ ለማዋል ዝግጅቱ ማጠናቀቁን መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም ዋና በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የሚመለከታቸው የስራ ክፍሎችና የድርጅቱ አመራሮች በተገኙበት ይፋ አደረገ፡፡
አቶ ዮናስ ዘለቀ የኢኢግልድ ተ/የዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ሃላፊ በመርሐግብሩ መክፈቻ ሥነ ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ኢኢግልድ በተሰጠው ተግባራትና ሃላፊነቶች መሰረት የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በማዘመንና በማሳላጥ የተገልጋዮችን ፍላጎት ለማርካት ትኩረት ሰጥቶ አየሰራ የሚገኝ እንደሆነና ይህም ሶፍትዌር እንዲለማ ሲደረግ በዋናነት አሰራሩንና አገልግሎት አሰጣጡን ከተገልጋዮች ፍላጎት አንጻር የተገናዘበ እንዲሆን ከፍተኛ ክትትል እንደተደረገበት ገልጸዋል፡፡
ስለዚህም በቀጥታ ከድርጅቱ ደንበኞች ጋር ግንኙነት ያላቸው የስራ ክፍሎች በተለይም በድርጅቱ የሚገኙ የሽያጭ ባለሙያዎች፣ የአስተዳደር ሥርዓቱን የሚመሩትና የሚከታተሉት የስራ ክፍሎች ትግበራውን በትኩረት እንዲያስፈጽሙ አሳስበዋል፡፡
በመርሐግብሩ ላይ የማርኬቲንግ፤ ደንበኞች አገልግሎትና ዲስትሪክት ዘርፍ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች፤ የኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ሃላፊና ባለሙያዎች እንዲሁም የሽያጭ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡



