ዜና
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅትና የኢትዮጵያ ፖስታ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሠነድ ተፈራረሙ
23/10/2024
በኢንዱስትሪ ግብዓቶች አቅርቦት ተግዳሮቶችና መፍትሄ ላይ ውይይት ተካሄደ
14/10/2024
እንኳን ደስ አላችሁ!!!
11/10/2024
ኢኢግልድ ላገኘው የ2016 በጀት ዓመት ስኬታማ አፈጻጸም ለአመራሮቹና ሠራተኞቹ እውቅና ሰጠ
26/08/2024
ኢኢግልድ የአቢሲኒያ ኢንዱስትሪዎች ሽልማት ከፍተኛ ተሸላሚ ሆነ
22/07/2024
የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታ አስተዳደርና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሃላፊዎች የችግኝ ተከላ አካሄዱ
20/07/2024
የማዕከላዊና የምዕራብ ዲስትሪክት ጽ/ቤቶች አስር ወራት ዕቅድ አፈጻጸምና 2017 የኮርፖሬት ዕቅድ ግምገማ ተካሄደ
20/05/2024
ኢኢግልድ በስትራቴጂክ ዕቅዱና በአሰራር መመሪያዎች ረቂቅ ላይ ሲያካሂድ የነበረውን ግምገማ አጠናቀቀ
13/05/2024
ኢኢግልድ ስትራቴጂክ ዕቅዱና ሌሎችም የአሰራር ስርዓቶቹን እየገመገመ ይገኛል
10/05/2024
ኢኢግልድ በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ላይ ተሳተፈ
09/05/2024
ኢኢግልድ 10ኛው አገር ዓቀፍ የሕብረት ሥራ ማሕበራት ኤግዚቢሽንና ባዛር ተሳተፈ
15/02/2024
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በኢኢግልድ ጉብኝት አካሄዱ
29/01/2024
የአመራሮችና የባለሙያዎች ቅንጅትና የስራ ትጋት ለድርጅቱን አፈጻጸም ውጤታማነት ሚና እንደሚኖረው ተገለጸ
17/01/2024
ማስታወቂያ
27/11/2023
የምግብ ዘይት በቫይታሚን ለማበልጸግ የሚያስፈልገውን የፕሪሚክስ አቅርቦትን አስመልክቶ የወጣ ማስታወቂያ
06/11/2023
ኢኢግልድ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ገመገመ
06/11/2023
ማስታወቂያ
25/10/2023
ኢኢግልድ የ4.2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አበረከተ
17/10/2023
ኢኢግልድ የ16.5 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት በተመጣጣኝ ዋጋ አቀረበ
14/09/2023
ኢኢግልድ የዲስትሪክቶችን የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የቀጣይ ዓመት ዕቅድ ግምገማ አካሄደ
23/08/2023
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅትና የኢትዮጵያ ፖስታ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሠነድ ተፈራረሙ
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅትና የኢትዮጵያ ፖስታ ድርጅት ያሏቸውን የመሠረተ ልማቶችና በጋራ ተጠቃሚ በሚያደርጓቸው የአሰራር ስርዓቶች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ጥቅምት 14 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ፖስታ ጽ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተፈራረሙ፡፡
በፊርማ ስነሥርዓቱ የኢኢግልድ የኢንዱስትሪ ውጤቶች ግዢና ሽያጭ ዘርፍ ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አበባዬ ገዛኸኝ እንዲሁም በኢትዮጵያ ፖስታ የንግድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ትዕግስት በቀለ ድርጅቶቻቸውን በመወከል የመግባቢያ ሰነዱን ተፈራርመዋል፡፡
የኢትዩጵያ ፖስታ የረጅም ዓመታት ልምድና በመላ አገሪቱ 700 የሚጠጉ ቅርንጫፎች ያሉት የመንግስት የልማት ድርጅት ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ከ85 ዓመታት በላይ በንግዱ ዘርፍ የቆየና በመላ አገሪቱ 83 የሽያጭ ቅርንቻፎች ያሉት ድርጅት እንደሆነ በሁለቱም ድርጅቶች የበላይ አመራሮች ተነስቷል፡፡
ሁለቱም ድርጅቶች ያሏቸውን ይህንን እምቅ አቅም በመጠቀም ድርጅቶቻቸው የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች ማማሳደግና ማሻሻል የሚቻልበትን አሰራር መዘርጋት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶ ወደ ስራ እንደተገባም የተገለጸ ሲሆን ይህም ድርጅቶቹ ያሏቸውን የመሠረተ ልማቶችና ያሏቸውን የአሰራር ስርዓቶች በመጋራት የድርጅቶቻቸውን ተጠቃሚነት ማረጋገጥና የሀገርን ሐብት በአግባቡ ሥራ ላይ ማዋል ተገቢ እንደሆነ የድርጅቶቹ አመራሮች በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ አመላክተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ግብዓት የሚያቀርብና ያመረቷቸውን ምርቶችም ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያቀርብ የመንግስት የልማት ድርጅት ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ የኢትዮጵያ ፖስታ ደግሞ በአገራችን የፖስታ፣ የሎጀሰቲክስና ትራንስፖርት፣ የመንገድ ፈንድ ክፍያ፣ የብሔራዊ መታወቂያ እና የሰርተፍኬት ዕድሳት አገልግሎቶችን የሚሰጥ የመንግስት የልማት ድርጅት እንደሆነ ይታወቃል፡፡