የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የተጀመረውን የከይዘን የአሰራር ሥርዓት አጠናክሮ ለማስቀጠል እንዲቻል የባላይና መካከለኛ አመራሮች የተሳተፉበት የአንድ ቀን ስልጠና በኢትዮጵያ ከይዘን ኢንስቲትዩት ባለሙያዎች የካቲት 11 ቀን 2011 ዓ.ም በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተሰጠ፡፡

የስልጠናው ዓላማ የከይዘን የአሰራር ስርዓት ትግበራ ትኩረት አንዲሰጠውና ክትትልና ግምገማ ተጠናክሮ እንዲካሄድ በማድረግ የተቀዛቀዘውን የከይዘን ትግበራ ማቀጣጠልና አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሆነ የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወንዳለ ሀብታሙ በሠልጠናው መክፈቻ ላይ አመልክተዋል፡፡

አያይዘውም የከይዘንን ትግበራ የበላይ አመራሩ በባለቤትነት ተቀብሌ ተግባራዊ ለማድረግ በቁርጠኝነት ካልሰራ ወደሚጠበቀው ግብ ለመድረስ አስቸጋሪ እንደሚሆን አሳስበዋል፡፡

ኢግልድ የከይዘንን ትግበራ በሙከራ ደረጃ በአራት ዳይሬክቶሬቶች ማለትም በፋይናንስ፤ በአስተዳደር፤ በሎጀስቲክስና በሽያጭ ዳይሬክቶሬቶች የተጀመረ ቢሆንም የድርጅቱ የበላይ አመራሮች የተሰጠው ትኩረት አናሳነትና የክትትልና ግምገማ ስርዓት ዝቅተኛ መሆን እንዲሁም የከይዘን ኢንስቲትዩት ድጋፍ የተቆራረጠና የባለሙያዎች መቀያየር የፈጠሩት ችግሮች የተጠበቀውን ውጤት ለማምጣት እንቅፋት መሆናቸው ታውቋል፡፡

ከዚህ ሥልጠና በኋላ የበላይ አመራሩ ሃላፊነት በመቀበል የከይዘንን ትግበራ በበላይነት የመምራት፤የመገምገምና የመከታተል ሃላፊነት በመውሰድ  ዕቅዱን ከግብ ለማድረስ እንደሚሰራ የሚጠበቅ መሆኑም ተገልጿል፡፡  

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የፌደራል የህብረት ስራ ኤጀንሲ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ባዘጋጀው 2011 ስድስተኛው ዙር አገር ዓቀፍ የህብረት ሥራ ኤግዚቢሽን ፣ባዛርና ሲምፖዚየም በመሳተፍ ላይ ይገኛል፡፡


ኢግልድ በኢግዚቢሽኑ ልዩ ልዩ ግብዓቶችን ይዞ እየተሳተፈ ሲሆን በዚህ ዓይነቱ መድረክ መካፈል ድርጅቱ የሚያቀርባቸውን ግብዓቶች ለህብረት ስራ ማህበራት ለማስተዋወቅና የተጠናከረ ትስስር ለመፍጠር ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡

Latest News