በኢግልድ 83 የሽያጭ ቅርንጫፎች የሚሠሩ የሽያጭና የመጋዘን ሃላፊዎች በትራናስፎርሜሽናል አመራር፤ በአስተዳደር፤ በሽያጭ ክህሎትና በደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ግምገማዊ ስልጠና ከየካቲት 1 ቀን 2011 . ጀምሮ በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጀመረ፡፡

በሥልጠናው መክፈቻ ላይ የድርጅቱ የሰው ሃይል ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት ስራ አስፈጻሚ አቶ ሳሙኤል መላኩ እንደገለጹት የሥልጠናው ዓላማዎች በድርጅቱ ውስጥ በተሻለ ደረጃ እየሰሩ ያሉ ቅርንጫፍ ሃላፊዎችን የአመራር ክህሎት ማጠናከር፤ በድርጅቱ ተልዕኮ፤ ራዕይና ስራዎች ላይ የጋራ ግንዛቤ መፍጠርና የቅርንጫፍ ሃላፊዎች ሲያከናውኑ የነበሩትን ተግባራት መልሰው እንዲያዩትና ሊስተካከሉ የሚገቡ የተዛነፉ አሰራሮችን እንዲያስተካክሉ ማድረግ ነው፡፡

በተጨማሪም በኦዲት ስራ ፤በህንጻና ሎጀስቲክስ አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት፤በህግ ጉዳዮች እንዲሁም በግዢና በሽያጭ አፈጻጸም ችግሮችና የመፍትሄ ሃሳቦች ዙሪያ በየስራ ክፍሉ ሃለፊዎች የመነሻ ጽሁፎች ቀርበው ሰፊ ውይይት የካሄድባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

 

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት 2011 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት 485 ሜትሪክ ቶን የተዳመጠ ጥጥ፤ 65 ሺህ ካሬ ያለቀለት ቆዳና 14716 ኩንታል የኢንዱስትሪ ጨው ለአምራች ኢንዱስትሪዎች በግብዓትነት አቀረበ፡፡

ይህ የተገለጸው ድርጅቱ የበጀት ዓመቱን የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸምና የቀጣዩን የመቶ ቀናት ዕቅድ ከባለድርሻ አካላት ጋር ለመገምገም ጥር 30 ቀን 2011 . በግዮን ሆቴል ሳባ አዳራሽ ባለድሻ አካላት በተሳተፉበት የግማሽ ቀን የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ዮሐንስ ድንቅአየሁ የውይይት መድረኩን ሲከፍቱ ባደረጉት ንግግር በሀገራችን እየተካሄደ ያለውን ለውጥ ተከትሎ አሁን ኢትዮጵያ ላይ በተጀመረው የኢኮኖሚ ዕድገት አቅጣጫ መንግስት ለኢንዱስትሪው ዘርፍ ድጋፍ በመስጠትና በማበረታታት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

አያይዘውም ኢግልድ ባለፉት ዓመታት የሀገሪቱን ኢንዱስትሪዎች በግብዓት በመደገፍ የበኩሉን ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ አመልክተው ሆኖም ግን በአፈጻጸም ሂደት ተግዳሮት እየገጠመው እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

ሚኒስትር ዲኤታው በዋናነት እንዳስቀመጡት ከመንግስት ለመቋቋሚያ የተፈቀደለት የመስሪያ ካፒታል ብር 792 ሚሊዮን አለመለቀቅና ድርጅቱ ለመሠረታዊ ሸቀጥ ያወጣው ብር 580 ሚሊዮን አለመመለስ በድምሩ 1.3 ቢሊዮን ከመንግስት አለመከፈሉ በድርጅቱ አፈጻጸም ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡

ችግሩንም ለመፍታት ጉዳዩን የንግድን ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲያውቁት በሪፖርት መልክ የቀረበ ሲሆን በቀጣይ የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር ምላሽ ይሰጥበታል ተብሎ እንደሚጠበቅም አመልክተዋል፡፡

የኢግልድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወንዳለ ሀብታሙ በበኩላቸው በውይይት መድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በጨርቃጨርቅ፤ በቆዳና በአግሮፕሮሰሲንግ ዘርፍ ለተሰማሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድሰት ወራት የተለያዩ ግብዓቶችን የማቅረብ ስራዎች እንደተሰሩ ገልጸው በዋናነትም የተዳመጠ ጥጥ፤ ቆዳና የኢንዱስትሪ ጨው ለአምራች ኢንዱስትሪዎች እንዲቀርብ ተደርጓል፡፡

አያይዘውም በሌሎችም የኢንዱስትሪ ዘርፎች ስራዎች በሂደት ላይ እንደሚገኙ አመልክተው ከኬሚካል አቅርቦት ጋር በተያያዘ ከኢንዱስትሪዎች በቀረበ ጥያቄ መሠረት 48 የቆዳ ኬሚካሎች ተለይተው ዓለም አቀፍ ጨረታ ወጥቶ አሸናፊዎችን የመለየት ስራ እንደተሰራ፤ በብረታብረት ዘርፍ ደግሞ ከብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር በመቀናጀት የፋብሪካዎችን ፍለጎት ተጠንቶ ዓለም ዓቀፍ ጨረታ በማውጣት ሂደት ላይ እንደሚገኝ ተብራርቷል፡፡

የውይይት መድረኩ ከላይ የተጠቀሱትንና ሌሎችንም ተጓዳኝ ጌዳዮች በስፋት የገመገመ ሲሆን ባለድርሻ አካላትም በቀረበው ሪፖርትና ዕቅድ ዙሪያ አስተያየቶቻቸውንና ጥያቄዎቻቸውን አቅርበው ከሚመለከቷቸው አካላት ምላሽ ተሰጥቷቸው የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

Latest News