ኢግልድ በፌዴራል ከተሞች የስራ እድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ባዘጋጀው ኢግዚቢሽንና ባዛር ላይ ተሳተፈ፡፡

ኢግልድ "ውጤታማ የሀገር ውስጥ የገበያ ትስስር ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ዘላቂ ዕድገት" በሚል መሪ ቃል በፌዴራል  ከተሞች  የስራ  እድል  ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ በተዘጋጀውና ከታህሳስ 20 እስከ ታህሳስ 26 ቀን 2010 .ም ድረስ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው ኤግዚቢሽን ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛል፡፡

ድርጅቱ በኢግዝብሽንና ባዛሩ ላይ መሳተፉ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች ያሉት ሲሆን በተለይም   ድርጅቱ የሚያቀርባቸውን የኢንዱስትሪ ግብዓቶችንና ውጤቶችን በማስተዋወቅ፤ የገበያ ትስስር መፍጠርና ምርቶቹን በመሸጥ ተጠቃሚ እንደሚሆን የጠበቃል፡፡ በኢግዝቪሽንና ባዛሩ ላይ ድርጅታችን ካቀረባቸው የኢንዱስትሪ ግብዓቶችና ውጤቶች መካከል ከኢንዱስትሪ ግብዓቶች ጥጥ፤የተለያ ቆዳዎችና ጨው እንዲሁም  ከኢንዱስትሪ ውጤቶች ሳሙና፣ ጎማ፣ አርማታ ብረት ቆርቆሮና ሚስማር፣ አንሶላ፤ ብርድልብስና የተለያዩ አልባሳት መሆናቸው ታውቋል፡፡

የመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት ክቡር ዶ/ር አምባቸው መኮንን የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር ሚኒስትር እንደተናገሩት እየተካሄደ ባለው ኤግዚቢሽንና ባዛር ላይ የሚሳተፉት ኢንተርፕራይዞች በትጋት ሰርተው ከድህነት መላቀቅ እንደሚቻል  በተጨባጭ ካረጋገጡ ኢንተርፕራይዞች መካከል የተመረጡ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በተዘጋጀው አንደኛ ዙር ሀገር አቀፍ የሞዴል ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ኤግዚቢሽንና ባዛር ዝግጅት ላይ ከሁሉም የሀገሪቱ ክልልች እና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ 167 ሞዴል ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ተሳታፊ መሆናቸው በዝግጅቱ ወቅት ተብራርቷል፡፡

ከነዚህም ውስጥ 113 የሚሆኑት በሴቶች ባለቤትነት የሚመሩ ኢንተርፕራይዞች ሲሆኑ፤ሶስት ኢንተርፕራይዞች ደግሞ በአካል ጉዳተኞች ባለቤትነት የሚመሩ መሆናቸውን ለመረዳት ተችሏል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በኤግዚቢሽኑ 25 በአጋር አካላት የተመለመሉ ኢተርፕራይዞች የሚገኙ ሲሆን፣ በጠቅላላው 192 ኢተርፕራይዞች ተሳትፈዋል፡፡

ከባዛሩና ኤግዚቢሽኑ ከ15,000 ሺ በላይ የሚሆኑ ተጠቃሚ የህብረተሰብ ክፍል እንደሚጎበኝ እና የ4 ሚሊዮን ብር የገብያ ትስስር እና ሽያጭ እንደሚፈጠር ይጠበቃል፡፡

 

Save

Save

Latest News