የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች የሚታየውን የሲሚንቶ ዋጋ ንረት ለማረጋጋት ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተሠጠውን ሃለፊነት መሠረት በማድረግ ከተለያዩ ፋብሪካዎች የሲሚንቶ ምርቶችን በመረከብ በተመጣጣኝ ዋጋ ለተጠቃሚዎች በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡

በዚህም መሠረት በቅድሚያ  በአዲስ አበባ በሚገኙ የድርጅታችን ሦስት የሽያጭ ቅርንጫፎች ማለትም በቃሊቲ፣ በአብነትና  በኮልፌ  ቅርንጫፎች  የደርባ፣ የዳንጎቴ፤ የሐበሻና የሙገር ሲሚንቶ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ያቀረበን ሲሆን የመሸጫ ዋጋቸውም ብር ፡-

1.  ደርባ ሲሚንቶ                      234.59 ብር

2.  የዳንጎቴ ሲሚንቶ                    255.00 ብር

3.  የሐበሻ ሲሚንቶ                     251.03 ብር

4.  የሙገር ሲሚንቶ                    236.92 ብር

ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡

በተጨማሪም ከደንበኞቻችን የቀረቡልንን አስተያየቶች መነሻ አድርገን ቀደም ባሉት ሣምንታት እየተሠራበት የነበረውን የሲሚንቶ ሽያጭና ሥርጭት ማስፈጸሚያ ፕሮሲጀር ማንዋል በመከለስ ተጠቃሚ ደንበኞቻችን ማሟላት የሚገባቸውን መስፈርቶች እንዲሁም መካተት የሚገባቸውንና ያልተካተቱትን  ተቋማትና ድርጅቶች በማካተት ማሻሻያ ያደረግን መሆኑን እየገለጽን ለተጨማሪ መረጃ የፌስ ቡክ ገጻችንን This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ይጎብኙ፡፡

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት

በከባድ ተሸከርካሪዎች ላይ የሚያገለግሉ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት 11 ሹፌሮች ከህዳር 1 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ የክህሎት ማሻሻያ ሥልጠና በድርጅቱ ዋና መ/ቤትና በቃሊቲ የሽያጭ ቅርንጫፍ ቅጥር ጊቢ ውስጥ እየተሰጠ ይገኛል፡፡

የሥልጠናው ዓላማዎች የሹፌሮቹን አቅምና ክህሎት ለማዳበር፣ የትራፊክ አደጋዎችን ለመቀነስ እየተሰራ የሚገኘውን አገራዊ እቅስቃሴ ለመደገፍና ድርጅቱ በቅርቡ በግዢ በሚያስገባቸው ከባድ ተሸከርካሪዎች ላይ የተሻለ ብቃት እንዲኖራቸው ለማስቻል እንደሆነ ታውቋል፡፡

በተያያዘም ሹፌሮች የቴክኒክና የንድፈ ሐሳብ ክህሎቶቻቸውን ለማዳበር እንዲችሉ በደህንነት ትግበራ፣ በተሸከርካሪዎች ሜካኒካልና ቴክኒካል ስርዓቶች እንዲሁም ሹፌሮች ሊኖራቸው በሚገባ ባህሪያትና ሌሎችም ተግባር ላይ ትኩረት ያደረጉ ስልጠናዎች እየተሰጠ ይገኛል፡፡

ሥልጠናው በሰው ሐብት ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት የአቅም ግንባታ ቡድን  የድርጅቱን ሠራተኞች አቅም በስልጠና በማገዝ የድርጅቱንና የሠራተኞችን  የመፈጸም አቅም ለማሳደግ ያዘጋጀው መርሃ ግብር አካል እንደሆነም ተገልጿል፡፡  

Latest News