በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት በአዲስ አበባና በአካባቢዋ ከተሞች በሚገኙ የሽያጭ ቅርንጫፎች ለሚሰሩ የቅርንጫፍና የመጋዘን ሃላፊዎች የድርጅቱን የሽያጭ ስራዎች ለማሳለጥ የሚያስችል ስልጠና ህዳር 9 ቀን 2012 ዓ.ም በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽና በክልል ከተሞች እየተሰጠ ይገኛል፡፡

አቶ ደጀኑ ተ/ማርያም የኢግልድ የሽያጭ ዘርፍ ም/ ዋና ስራ አስፈጻሚ በስልጠናው ወቅት እንደገለጹት በአሁኑ ወቅት ኢኢግልድ የመንግስትን ፖሊሲ ከማስፈጸም አኳያ ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው ድርጅት ሲሆን በተለይም ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ከሚታይባቸው መሰረታዊ ሸቀጦች መካከል የምግብ ዘይት አንዱ ሲሆን ምርቱንም ለህብረተሰቡ እንዲያቀርብና በመላ አገሪቱ እንዲያሰራጭ ተወስኖ ወደስራ ተገብቷል፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ የህብረተሰቡ ወርሃዊ የምግብ ዘይት ፍለጎት 40 ሚሊዮን ሊትር እንደሆነና ከዚህ ውስጥ 33 ሚሊዮን ሊትር ኢኢግልድ በግዢ እንዲያስገባና እንዲያሰራጭ እንደተወሰነ የገለጹት አቶ ደጀኑ ከዚህም በተጨማሪ በሲሚንቶ ዋጋ ላይ የሚታየውን የዋጋ ግሽበት ለመቆጣጠርና ገበያውን ለመረጋጋት በተመሳሳይ መልኩ ሃላፊነት ወሰዶ እንዲያሰራጭ ተወሰኖ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀው ወደስራ ለመግባት እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

አያይዘውም ድርጅቱ ይህንን የሽያጭ  ስራ በሚያከናወነወበት ወቅት ከወዲሁ ተገቢውን ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በመረዳት ከስራው ጋር በቀጥታ ግንኙነት ያላቸውን የሽያጭ ቅርንጫፍና የመጋዘን ሃላፊዎች በምርት ቅበላና እደላ፤ በደንበኞች አያያዝ፣ አገልግሎት አሰጣጥና ቅሬታ አቀራረብ እንዲሁም ሪፖርት ቀራረብና ሠነድ ቅብብሎሽ ላይ ትኩረት ተደርጎ ይህ ሥልጠና እንደተዘጋጀና ጠቀሜታውም የጎላ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

በማጠቃለያም ኢኢግልድ በመንግስት የተሰጠውን ሃላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ የቀድሞ ልምዱንና በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተዘጋጀውን የንግድ መመሪያ መሠረት በማድረግ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ አሳስበው ሥልጠናው የሽያጭ ቅርንጫፍና የመጋዘን ሃላፊዎችን አቅም በመገንባት ጠቀሜታው ከፍተኛ እንደሆነ አሳስበዋል፡፡

ሥልጠናው አዲስ አበባን፤ በጎንደርን፣ በደብረማርቆስን፤ መቀሌን፣ ጂማን፣ ነቀምትን፣ ከምቦልቻን፣ ድሬዳዋን፣ ሻሸመኔንና ወላታ ሶዶን ከተሞችን የማሰልጠኛ መዕከል በማድረግ በአቅራቢያቸው የሚገኙትን የሽያጭ ቅርንጫፎችን በማካተት ከህዳር 9-12/2012 በመሰጠት ላይ፡፡

ኢኢግልድ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ዓመታት በየወሩ 27 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት በ37 የሽያጭ ቅርንጫፎችና፤ በእያንዳንዱ ዙር 400 ሺህ ኩንታል ስኳር በ69 የሽያጭ ማዕከሎች በማሰራጨት ሃላፊነቱን የተወጣ የመንግስት የልማት ድርጅት ነው፡፡     

በከባድ ተሸከርካሪዎች ላይ የሚያገለግሉ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት 11 ሹፌሮች ከህዳር 1 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ የክህሎት ማሻሻያ ሥልጠና በድርጅቱ ዋና መ/ቤትና በቃሊቲ የሽያጭ ቅርንጫፍ ቅጥር ጊቢ ውስጥ እየተሰጠ ይገኛል፡፡

የሥልጠናው ዓላማዎች የሹፌሮቹን አቅምና ክህሎት ለማዳበር፣ የትራፊክ አደጋዎችን ለመቀነስ እየተሰራ የሚገኘውን አገራዊ እቅስቃሴ ለመደገፍና ድርጅቱ በቅርቡ በግዢ በሚያስገባቸው ከባድ ተሸከርካሪዎች ላይ የተሻለ ብቃት እንዲኖራቸው ለማስቻል እንደሆነ ታውቋል፡፡

በተያያዘም ሹፌሮች የቴክኒክና የንድፈ ሐሳብ ክህሎቶቻቸውን ለማዳበር እንዲችሉ በደህንነት ትግበራ፣ በተሸከርካሪዎች ሜካኒካልና ቴክኒካል ስርዓቶች እንዲሁም ሹፌሮች ሊኖራቸው በሚገባ ባህሪያትና ሌሎችም ተግባር ላይ ትኩረት ያደረጉ ስልጠናዎች እየተሰጠ ይገኛል፡፡

ሥልጠናው በሰው ሐብት ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት የአቅም ግንባታ ቡድን  የድርጅቱን ሠራተኞች አቅም በስልጠና በማገዝ የድርጅቱንና የሠራተኞችን  የመፈጸም አቅም ለማሳደግ ያዘጋጀው መርሃ ግብር አካል እንደሆነም ተገልጿል፡፡  

Latest News