የኢግልድ ሠራተኞችና አመራሮች የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሔዱ (01)

የኢትዮጵየ ኢንዱስትሪ ግብዓት ልማት ድርጅት አመራሮችና ሠራተኞችአንድ ችግኝ ለታላቁ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ በሚል መሪ ቃል ልዩ ስም ሽንቁሩ ሚካኤል አካባቢ በተባለ ሥፍራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ነሐሴ 9 ቀን 21 / አከናወኑ፡፡

 

 

 
በዚህ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ማጠናቀቂያ ላይ የኢግልድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ወንዳለ ሀብታሙ የአገራችን የደን ሽፋን ተራቁቶ ለከፍተኛ ሥጋት ተዳርጋ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታ እንደነበር ገልፀው ይህ አደጋ እንዲቀለበስ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተጀመረው የሕዝብ ተሣትፎ እንቅስቃሴ አመርቂ ውጤት መገኘቱን አመልክተዋል፡፡ 


በዚህም መሠረት የአገራችን የደን ሀብት ከነበረበት 3 በመቶ ወደ 15 በመቶ ከፍ ማለቱን የገለፁት ዋና ሥራአስፈጻሚው የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅትም የደን ልማት አገራዊ ንቅናቄ ከተጀመረበት ጊዜ ወዲህ በተለያዩ ሥፍራዎች የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በማዘጋጀት የአረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ አካል በመሆን ተሳታፊ እንደነበር አሳስበው ይህ ጥረት ከሌላው የአረንጓዴ ልማት ሥራዎች ጋር ተዳምሮ የአገሪቱን የካርቦን ልቀት መጠን ዝቅ እንዲል የሚያስችል እንደሆነም አመልክተዋል፡፡ በዚህም የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የኢግልድ ዋና /ቤት አመራርና ሠራተኞች የተሳተፉ ሲሆን በአጠቃላይ 15ዐዐ የሚደርሱ የተለያዩ ችግኞች ተተክለዋል፡፡ በቀጣይም የተተከሉት ችግኞችን የመንከባከብ ሥራዎች እንዲሠሩ የደን ልማት ባለሙያው ባመለከቱት መሠረት የድርጅቱ ሠራተኞች በቀጣይ የተተከሉትን ችግኞች የራሳቸውን መርሃ ግብር በማዘጋጀት እንደሚንከባከቧቸው በድርጅቱ በኩል ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

Latest News