የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት በ9ኛው ሀገር አቀፍ የህብረት ስራ ኤግዚቢሽንና ባዛር ላይ በመሳተፍ ምርትና አገልግሎቱን አስተዋወቀ።
የካቲት 2 ቀን 2014 ዓ.ም የተከፈተው ኤግዚቢሽንና ባዛር ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች መጡ ከ150 በላይ የህብረት ስራ ማህበራት የተለያዩ የግብርናና ሌሎችም ምርቶቻቸውን በማቅረብ ከተለያዩ የንግዱ ማህበረሰብ ጋር የገበያ ትሥሥር ለመፍጠር ሁኔታዎችን የሚፈጥርላቸው መድረክ ሲሆን በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት በገበያው ላይ የሚታየውን የዋጋ ንረት ለመርገብም አስተዋጽኦው ከፍተኛ ነው፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘም ኢኢግልድ በዚሁ የህብረት ስራ ኤግዚቢሽንና ባዛር የንግድ ለንግድ ግንኙነት ( )በመፍጠር በአግሮ-ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለተሰማሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች የግብርና ምርቶችን በማቅረብ ኢንዱስትሪዎችን ለመደገፍ የሚያስችሉትን የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ለማከናወን እየሰራ ይገኛል፡፡